የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዮሐንስ 19:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም የእ​ሾህ አክ​ሊል ደፍቶ፥ የቀይ ሐር መጐ​ና​ጸ​ፊ​ያም ለብሶ ወደ ውጭ ወጣ፤ ጲላ​ጦ​ስም፥ “እነሆ፥ ሰው​ዬው” አላ​ቸው።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ኢየሱስ የእሾኽ አክሊል ደፍቶ ሐምራዊ ልብስም ለብሶ ወጣ፤ ጲላጦስም፣ “እነሆ፤ ሰውየው!” አላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ኢየሱስም የእሾህ አክሊል ደፍቶ፥ ቀይ ልብስም ለብሶ፥ ወደ ውጭ ወጣ። ጲላጦስም “እነሆ ሰውዬው፤” አላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ስለዚህ ኢየሱስ የእሾኽ አክሊል ደፍቶና ቀይ ልብስ ለብሶ ወደ ውጪ ወጣ፤ ጲላጦስም “እነሆ፥ ሰውየው!” አላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ኢየሱስም የእሾህ አክሊል ደፍቶ ቀይ ልብስም ለብሶ ወደ ውጭ ወጣ።

ምዕራፉን ተመልከት



ዮሐንስ 19:5
8 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ለጽ​ዮን የም​ሥ​ራ​ችን የም​ት​ነ​ግር ሆይ፥ ከፍ ወዳ​ለው ተራራ ውጣ፤ ለኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የም​ሥ​ራ​ችን የም​ት​ነ​ግር ሆይ፥ ድም​ፅ​ህን በኀ​ይል አንሣ፤ አት​ፍራ፤ ለይ​ሁ​ዳም ከተ​ሞች፦ እነሆ፥ አም​ላ​ካ​ችሁ! ብለህ ንገር።


አሁ​ንም ያዕ​ቆብ ሆይ፥ የፈ​ጠ​ረህ፥ እስ​ራ​ኤ​ልም ሆይ፥ የሠ​ራህ እግ​ዝ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ተቤ​ዥ​ች​ሃ​ለ​ሁና አት​ፍራ፤ በስ​ም​ህም ጠር​ቼ​ሃ​ለሁ፤ አንተ የእኔ ነህ።


ስለ​ዚህ ጌታ ራሱ ምል​ክት ይሰ​ጣ​ች​ኋል፤ እነሆ፥ ድን​ግል ትፀ​ን​ሳ​ለች፤ ወንድ ልጅ​ንም ትወ​ል​ዳ​ለች፤ ስሙ​ንም አማ​ኑ​ኤል ብላ ትጠ​ራ​ዋ​ለች።


ላሜድ። እና​ንተ መን​ገድ ዐላ​ፊ​ዎች ሁሉ! በእ​ና​ንተ ዘንድ ምንም የለ​ምን? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጽኑ ቍጣው ቀን እኔን እን​ዳ​ስ​ጨ​ነ​ቀ​በት በእኔ ላይ እንደ ተደ​ረ​ገው እንደ እኔ ቍስል የሚ​መ​ስል ቍስል እን​ዳለ ተመ​ል​ከቱ፤ እዩም።


ከእሾህም አክሊል ጐንጕነው በራሱ ላይ፥ በቀኝ እጁም መቃ አኖሩ፤ በፊቱም ተንበርክከው “የአይሁድ ንጉሥ ሆይ! ሰላም ለአንተ ይሁን፤” እያሉ ዘበቱበት፤


በማ​ግ​ሥ​ቱም ዮሐ​ንስ ወደ እርሱ ሲመጣ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን አይቶ እን​ዲህ አለ፤ “እነሆ፥ የዓ​ለ​ሙን ኀጢ​ኣት የሚ​ያ​ስ​ወ​ግድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በግ።


ጭፍ​ሮ​ችም የእ​ሾህ አክ​ሊል ጐን​ጕ​ነው በራሱ ላይ ደፉ​በት፤ የቀይ ሐር መጐ​ና​ጸ​ፊ​ያም አለ​በ​ሱት።


የእ​ም​ነ​ታ​ች​ን​ንም ራስና ፈጻ​ሚ​ውን ኢየ​ሱ​ስን እን​ከ​ተ​ለው፤ እርሱ ነው​ርን ንቆ፥ በፊ​ቱም ስላ​ለው ደስታ በመ​ስ​ቀል ታግሦ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዙፋን ቀኝ ተቀ​ም​ጦ​አ​ልና።