የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዮሐንስ 16:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

“እኔ በእ​ው​ነት የሚ​ሆ​ነ​ውን እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ፤ እኔ ብሄድ ይሻ​ላ​ች​ኋል፤ እኔ ካል​ሄ​ድሁ ጰራ​ቅ​ሊ​ጦስ ወደ እና​ንተ አይ​መ​ጣ​ምና፤ እኔ ከሄ​ድሁ ግን እር​ሱን እል​ክ​ላ​ች​ኋ​ለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ነገር ግን፣ እውነት እላችኋለሁ፤ መሄዴ ይበጃችኋል። እኔ ካልሄድሁ አጽናኙ ወደ እናንተ አይመጣም፤ ከሄድሁ ግን እርሱን ወደ እናንተ እልካለሁ፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እኔ ግን እውነት እነግራችኋለሁ፤ እኔ ብሄድ ይሻላችኋል። እኔ ባልሄድ አጽናኙ ወደ እናንተ አይመጣምና፤ እኔ ብሄድ ግን እርሱን እልክላችኋለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እኔ ግን እውነት፥ እውነት እላችኋለሁ፤ የእኔ መሄድ ለእናንተ ይጠቅማችኋል፤ እኔ ካልሄድኩ አጽናኙ ወደ እናንተ አይመጣም፤ እኔ ከሄድኩ ግን እርሱን እልክላችኋለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እኔ ግን እውነት እነግራችኋለሁ፤ እኔ እንድሄድ ይሻላችኋል። እኔ ባልሄድ አጽናኙ ወደ እናንተ አይመጣምና፤ እኔ ብሄድ ግን እርሱን እልክላችኋለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት



ዮሐንስ 16:7
19 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ነፍ​ሴን ተመ​ል​ክ​ተህ ተቤ​ዣት፤ ስለ ጠላ​ቶ​ችም አድ​ነኝ።


እነሆ፥ እኔ የአ​ባ​ቴን ተስፋ ለእ​ና​ንተ እል​ካ​ለሁ፤ እና​ንተ ግን ከአ​ር​ያም ኀይ​ልን እስ​ክ​ት​ለ​ብሱ ድረስ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ከተማ ተቀ​መጡ።”


እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ በነ​ቢዩ በኤ​ል​ያስ ዘመን በም​ድር ሁሉ ብርቱ ረኃብ እስ​ኪ​ሆን ድረስ ሰማይ ሦስት ዓመት ከስ​ድ​ስት ወር በተ​ዘ​ጋ​በት ጊዜ ብዙ መበ​ለ​ቶች በእ​ስ​ራ​ኤል ውስጥ ነበሩ።


እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ በዚህ ከቆ​ሙት የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ግ​ሥት እስ​ኪ​ያ​ዩ​አት ድረስ ሞትን የማ​ይ​ቀ​ምሱ አሉ።”


ነገር ግን አብ በስሜ የሚ​ል​ከው የእ​ው​ነት መን​ፈስ ጰራ​ቅ​ሊ​ጦስ እርሱ ሁሉን ያስ​ተ​ም​ራ​ች​ኋል፤ እኔ የነ​ገ​ር​ኋ​ች​ሁ​ንም ሁሉ ያሳ​ስ​ባ​ች​ኋል።


እኔ እን​ደ​ም​ሄድ ወደ እና​ን​ተም እን​ደ​ም​መ​ለስ የነ​ገ​ር​ኋ​ች​ሁን ሰም​ታ​ች​ኋል፤ ብት​ወ​ዱ​ኝስ ወደ አብ በመ​ሄዴ ደስ ባላ​ችሁ ነበር፤ እርሱ አብ ይበ​ል​ጠ​ኛ​ልና።


ከሄ​ድ​ሁና ቦታ ካዘ​ጋ​ጀ​ሁ​ላ​ች​ሁም ዳግ​መኛ እመ​ጣ​ለሁ፤ እና​ን​ተም እኔ በአ​ለ​ሁ​በት ትኖሩ ዘንድ ወደ እኔ እወ​ስ​ዳ​ች​ኋ​ለሁ።


“እኔ ከአብ ዘንድ የም​ል​ክ​ላ​ችሁ ጰራ​ቅ​ሊ​ጦስ እር​ሱም ከአብ የሚ​ወጣ የእ​ው​ነት መን​ፈስ በመጣ ጊዜ፥ እርሱ ስለ እኔ ይመ​ሰ​ክ​ራል።


እር​ሱም በመጣ ጊዜ ዓለ​ምን ስለ ኀጢ​አ​ትና ስለ ጽድቅ፥ ስለ ፍር​ድም ይዘ​ል​ፈ​ዋል።


ይህ​ንም የሚ​ያ​ም​ኑ​በት ሰዎች ይቀ​በ​ሉት ዘንድ ስለ አላ​ቸው ስለ መን​ፈስ ቅዱስ ተና​ገረ፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ገና ስላ​ል​ከ​በረ መን​ፈስ ቅዱስ ገና አል​ወ​ረ​ደም ነበ​ርና።


ጴጥ​ሮ​ስም አፉን ከፈ​ተና እን​ዲህ አለ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሰው ፊት እን​ደ​ማ​ያ​ዳላ በእ​ው​ነት አየሁ።


አሁን ግን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀኝ ከፍ ከፍ ብሎና የመ​ን​ፈስ ቅዱ​ስን ተስፋ ከአብ ገን​ዘብ አድ​ርጎ ይህን ዛሬ የም​ታ​ዩ​ት​ንና የም​ት​ሰ​ሙ​ትን አፈ​ሰ​ሰው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ወ​ዱ​ትን ምር​ጦ​ቹን በበጎ ምግ​ባር ሁሉ እን​ደ​ሚ​ረ​ዳ​ቸው እና​ው​ቃ​ለን።


ቀላል የሆ​ነው የጊ​ዜው መከ​ራ​ችን ክብ​ር​ንና ጌት​ነ​ትን ለዘ​ለ​ዓ​ለም አብ​ዝቶ ያደ​ር​ግ​ል​ና​ልና።