የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዮሐንስ 16:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

አሁን ግን ወደ ላከኝ ወደ አብ እሄ​ዳ​ለሁ፤ ከእ​ና​ንተ አንዱ እንኳ፦ ‘ወዴት ትሄ​ዳ​ለህ?’ ብሎ አይ​ጠ​ይ​ቀ​ኝም።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“እንግዲህ ወደ ላከኝ እሄዳለሁ፤ ይሁን እንጂ ከእናንተ፣ ‘የምትሄደው የት ነው?’ ብሎ የሚጠይቀኝ የለም።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

“አሁን ግን ወደ ላከኝ እሄዳለሁ፤ ከእናንተም ‘ወዴት ትሄዳለህ?’ ብሎ የሚጠይቀኝ የለም።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አሁን ግን ወደ ላከኝ መሄዴ ነው፤ ሆኖም ከእናንተ ‘ወዴት ትሄዳለህ?’ ብሎ የሚጠይቀኝ የለም።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

አሁን ግን ወደ ላከኝ እሄዳለሁ ከእናንተም፦ “ወዴት ትሄዳለህ?” ብሎ የሚጠይቀኝ የለም።

ምዕራፉን ተመልከት



ዮሐንስ 16:5
15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ አብ ሁሉን በእጁ እንደ ሰጠው፥ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ወጣ፥ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ደ​ሚ​ሄድ ባወቀ ጊዜ፥


ስም​ዖን ጴጥ​ሮ​ስም፥ “ጌታ ሆይ፥ ወዴት ትሄ​ዳ​ለህ?” አለው፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ፥ “ወደ​ም​ሄ​ድ​በት አሁን ልት​ከ​ተ​ለኝ አት​ች​ልም፤ ኋላ ግን ትከ​ተ​ለ​ኛ​ለህ” አለው።


እኔ እን​ደ​ም​ሄድ ወደ እና​ን​ተም እን​ደ​ም​መ​ለስ የነ​ገ​ር​ኋ​ች​ሁን ሰም​ታ​ች​ኋል፤ ብት​ወ​ዱ​ኝስ ወደ አብ በመ​ሄዴ ደስ ባላ​ችሁ ነበር፤ እርሱ አብ ይበ​ል​ጠ​ኛ​ልና።


ስለ ጽድቅ፥ እኔ ወደ አብ እሄ​ዳ​ለ​ሁና፥ እን​ግ​ዲህ ወዲ​ህም አታ​ዩ​ኝ​ምና ነው።


“ጥቂት ጊዜ አለ፤ አታ​ዩ​ኝ​ምም፤ ደግ​ሞም ጥቂት ጊዜ አለ፤ እን​ደ​ገ​ናም ታዩ​ኛ​ላ​ችሁ፤ ወደ አብ እሄ​ዳ​ለ​ሁና።”


ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም እርስ በር​ሳ​ቸው፥ “ጥቂት ጊዜ አለ፤ አታ​ዩ​ኝ​ምም፤ ደግ​ሞም ጥቂት ጊዜ አለ፤ እን​ደ​ገ​ናም ታዩ​ኛ​ላ​ችሁ፥ ወደ አብ እሄ​ዳ​ለ​ሁና የሚ​ለን ይህ ነገር ምን​ድ​ነው?” ተባ​ባሉ።


ከአብ ወጣሁ፤ ወደ ዓለ​ምም መጣሁ፤ ዳግ​መ​ኛም ዓለ​ምን እተ​ወ​ዋ​ለሁ፤ ወደ አብም እሄ​ዳ​ለሁ።”


አሁን ግን ወደ አንተ እመ​ጣ​ለሁ፤ በእ​ነ​ር​ሱም ደስ​ታዬ ፍጹም ይሆን ዘንድ ይህን በዓ​ለም እና​ገ​ራ​ለሁ።


እኔ ልሠ​ራው የሰ​ጠ​ኸ​ኝን ሥራ ፈጽሜ በም​ድር ላይ አከ​በ​ር​ሁህ።


እን​ግ​ዲህ የሰው ልጅ ቀድሞ ወደ ነበ​ረ​በት ሲያ​ርግ ብታ​ዩት እን​ዴት ይሆን?


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ጥቂት ቀን አብ​ሬ​አ​ችሁ እኖ​ራ​ለሁ፤ ከዚ​ህም በኋላ ወደ ላከኝ እሄ​ዳ​ለሁ።


እር​ሱም የክ​ብሩ መን​ጸ​ባ​ረ​ቅና የመ​ልኩ ምሳሌ ሆኖ፥ ሁሉን በሥ​ል​ጣኑ ቃል እየ​ደ​ገፈ ኀጢ​አ​ታ​ች​ንን በራሱ ካነጻ በኋላ፥ በሰ​ማ​ያት በግ​ር​ማው ቀኝ ተቀ​መጠ።


የእ​ም​ነ​ታ​ች​ን​ንም ራስና ፈጻ​ሚ​ውን ኢየ​ሱ​ስን እን​ከ​ተ​ለው፤ እርሱ ነው​ርን ንቆ፥ በፊ​ቱም ስላ​ለው ደስታ በመ​ስ​ቀል ታግሦ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዙፋን ቀኝ ተቀ​ም​ጦ​አ​ልና።