ዮሐንስ 14:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በስሜ የምትለምኑት ነገር ቢኖር ያን አደርግላችኋለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ማንኛውንም ነገር በስሜ ብትለምኑኝ፣ እኔ አደርገዋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ማናቸውንም ነገር በስሜ ብትለምኑ እኔ አደርገዋለሁ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ማንኛውንም ነገር በስሜ ብትለምኑ እኔ አደርገዋለሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ማናቸውንም ነገር በስሜ ብትለምኑ እኔ አደርገዋለሁ። |
እኔ መረጥኋችሁ እንጂ እናንተ የመረጣችሁኝ አይደለም፤ እንድትሄዱ፥ ፍሬም እንድታፈሩ፥ ፍሬአችሁም እንዲኖር፤ አብንም በስሜ የምትለምኑት ነገር ቢኖር ሁሉን እንዲሰጣችሁ ሾምኋችሁ።
ያንጊዜም እኔን የምትለምኑኝ አንዳች የለም፤ እውነት እውነት እላችኋለሁ፤ በስሜ አብን ብትለምኑት ሁሉን ይሰጣችኋል።
ስለ እናንተ በኢየሱስ ክርስቶስ ከእግዚአብሔር ዘንድ ለእናንተ ስለተሰጣችሁ ጸጋ ዘወትር እግዚአብሔርን አመሰግነዋለሁ።