የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ኤርምያስ 42:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የአ​ም​ላ​ካ​ች​ንን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስለ​ም​ን​ሰማ መል​ካም እን​ዲ​ሆ​ን​ልን፥ መል​ካም ወይም ክፉ ቢሆን፥ አን​ተን ወደ እርሱ የም​ን​ል​ክህ የአ​ም​ላ​ካ​ች​ንን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል እን​ሰ​ማ​ለን” አሉት።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

አምላካችንን እግዚአብሔርን በመታዘዝ መልካም ይሆንልን ዘንድ ነገሩ ቢስማማንም ባይስማማንም፣ አንተን ወደ እርሱ የምንልክህን አምላካችንን እግዚአብሔርን እንታዘዛለን።”

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የአምላካችንን የጌታን ድምፅ በመስማታችን መልካም እንዲሆንልን፥ መልካም ወይም ክፉ ቢሆን፥ እኛ ወደ እርሱ የምንልክህን የአምላካችንን የጌታን ድምፅ እንሰማለን።”

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

መልካም ቢሆንም ባይሆንም ለአምላካችን ለእግዚአብሔር ቃል እንታዘዛለን፤ ወደ እርሱ የምንልክህም የአምላካችንን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ብናከብር ሁሉ ነገር የሚሳካልን በመሆኑ ነው።”

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የአምላካችንን የእግዚአብሔርን ቃል በመስማታችን መልካም እንዲሆንልን፥ መልካም ወይም ክፉ ቢሆን፥ አንተን ወደ እርሱ የምንልክህ የአምላካችንን የእግዚአብሔርን ቃል እንሰማለን አሉት።

ምዕራፉን ተመልከት



ኤርምያስ 42:6
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከት​ን​ሽ​ነቴ ጀምሮ ሁል​ጊዜ ተሰ​ለ​ፉ​ብኝ፤ ነገር ግን አል​ቻ​ሉ​ኝም።


የቃል ኪዳ​ኑ​ንም መጽ​ሐፍ ወስዶ ለሕ​ዝቡ አነ​በ​በ​ላ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያለ​ውን ሁሉ እን​ሰ​ማ​ለን፤ እና​ደ​ር​ጋ​ለ​ንም” አሉ።


ክፉ ምክ​ርን መክ​ረ​ዋ​ልና ለነ​ፍ​ሳ​ቸው ወዮ​ላት! እን​ዲ​ህም አሉ፥ “ጻድ​ቁን እን​ሻ​ረው፤ ሸክም ሆኖ​ብ​ና​ልና፤” ስለ​ዚህ የእ​ጃ​ቸ​ውን ሥራ ፍሬ ይበ​ላሉ።


በአ​ባ​ትህ ዝግባ አዳ​ራሽ ስለ ሠራህ በውኑ ትነ​ግ​ሣ​ለ​ህን? በውኑ አባ​ትህ አይ​በ​ላና አይ​ጠ​ጣም ነበ​ርን? ፍር​ድ​ንና ጽድ​ቅ​ንስ አያ​ደ​ር​ግም ነበ​ርን? በዚ​ያም ጊዜ መል​ካም ሆኖ​ለት ነበር።


የቃ​ር​ሔም ልጅ ዮሐ​ናን፥ የጭ​ፍራ አለ​ቆ​ችም ሁሉ፥ ሕዝ​ቡም ሁሉ በይ​ሁዳ ምድር ይቀ​መጡ ዘንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል አል​ሰ​ሙም።


ነገር ግን፦ ቃሌን ስሙ፤ እኔ አም​ላክ እሆ​ና​ች​ኋ​ለሁ፤ እና​ን​ተም ሕዝብ ትሆ​ኑ​ኛ​ላ​ችሁ፤ መል​ካ​ምም ይሆ​ን​ላ​ችሁ ዘንድ ባዘ​ዝ​ኋ​ችሁ መን​ገድ ሂዱ ብዬ በዚህ ነገር አዘ​ዝ​ኋ​ቸው።


እን​ግ​ዲህ ያ መል​ካም ነው ብዬ የማ​ስ​በው ነገር በውኑ አጥፊ ሆነኝ እላ​ለ​ሁን? አይ​ደ​ለም፤ ነገር ግን ኀጢ​አት ኀጢ​አት እንደ ሆነች በታ​ወ​ቀች ጊዜ ሞትን አበ​ዛ​ች​ብኝ፤ ከዚ​ያም ትእ​ዛዝ የተ​ነሣ ኀጢ​አ​ተ​ናው እን​ዲ​ታ​ወቅ፥ ኀጢ​አ​ትም ተለ​ይታ እን​ድ​ት​ታ​ወቅ ኦሪት መል​ካ​ሙን ከክፉ ልት​ለይ ተሠ​ር​ታ​ለች።


እን​ግ​ዲህ ምን እን​ላ​ለን? ኦሪት ኀጢ​አት ናትን? አይ​ደ​ለ​ችም፤ ነገር ግን ኦሪት ባት​ሠራ ኀጢ​አ​ትን ባላ​ወ​ቅ​ኋ​ትም ነበር፤ ኦሪት፥ “አት​መኝ” ባትል ኖሮም ምኞ​ትን ፈጽሞ ባላ​ወ​ቅ​ኋ​ትም ነበር።


የሥጋ ዐሳብ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጠላቱ ነውና፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሕግ ስለ​ማ​ይ​ገዛ፥ መፈ​ጸም አይ​ቻ​ለ​ውም።


አንተ ቅረብ፤ አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ለ​ውን ሁሉ ስማ፤ እም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለአ​ንተ የሚ​ና​ገ​ረ​ውን ሁሉ ለእኛ ንገ​ረን፤ እኛም ሰም​ተን እና​ደ​ር​ገ​ዋ​ለን።


ለእ​ነ​ርሱ፥ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ለል​ጆ​ቻ​ቸው መል​ካም ይሆ​ን​ላ​ቸው ዘንድ፥ እን​ዲ​ፈ​ሩኝ፥ ሁል​ጊ​ዜም ትእ​ዛ​ዜን ሁሉ እን​ዲ​ጠ​ብቁ እን​ዲህ ያለ ልብ ማን በሰ​ጣ​ቸው፥


በሕ​ይ​ወት እን​ድ​ት​ኖሩ፥ መል​ካ​ምም እን​ዲ​ሆ​ን​ላ​ችሁ፥ በም​ት​ወ​ር​ሱ​አ​ትም ምድር ዕድ​ሜ​አ​ችሁ እን​ዲ​ረ​ዝም፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ባዘ​ዛ​ችሁ መን​ገድ ሁሉ ሂዱ።”


ሕዝ​ቡም ኢያ​ሱን፥ “አም​ላ​ካ​ች​ንን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እና​መ​ል​ካ​ለን፤ ቃሉ​ንም እን​ሰ​ማ​ለን” አሉት።