የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ኤርምያስ 30:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፥ “የሚ​ያ​ስ​ፈራ ድምፅ ትሰ​ማ​ላ​ችሁ፤ ፍር​ሀት ነው እንጂ ሰላም አይ​ደ​ለም።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ ‘የፍርሀትና የሽብር ጩኸት ተሰምቷል፤ ሰላምም የለም።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ጌታ እንዲህ ይላልና፦ የሽብር ድምፅ ሰምተናል፤ የፍርሃት ነው እንጂ የሰላም አይደለም።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

“የሰላም ሳይሆን የመሸበርና የመርበድበድ ድምፅ ይሰማል፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ የሚያስፈራ ድምፅ ሰምተናል፥ የፍርሃት ነው እንጂ የሰላም አይደለም።

ምዕራፉን ተመልከት



ኤርምያስ 30:5
22 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በዚ​ያም ቀን እንደ ባሕር መት​መም ይተ​ም​ሙ​ባ​ቸ​ዋል፤ ወደ ምድ​ርም ይመ​ለ​ከ​ታሉ፤ ድቅ​ድቅ ጨለ​ማን ያያሉ፤ ይጨ​ነ​ቃ​ሉም።


እንደ ድብና እንደ ርግብ በአ​ን​ድ​ነት ይሄ​ዳሉ፤ ፍር​ድን እን​ጠ​ባ​በቅ ነበር፤ መዳ​ንም የለም፤ ከእ​ኛም ርቆ​አል።


ወራ​ዶች ወደ ዱር ሁሉ መጥ​ተ​ዋል፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰይፍ ከም​ድር ዳር ጀምሮ እስከ ምድር ዳር ድረስ ይበ​ላ​ልና፤ ለሥጋ ለባሽ ሁሉ ሰላም የለም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማሰ​ማ​ር​ያ​ቸ​ውን አጥ​ፍ​ቶ​አ​ልና የእ​ረ​ኞች ጩኸት ድምፅ፥ የበ​ጎች አው​ራ​ዎ​ችም ልቅሶ ሆኖ​አል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ስ​ራ​ኤ​ልና በይ​ሁዳ ላይ የተ​ና​ገ​ረው ቃል ይህ ነው።


ፈር​ተው ወደ ኋላ ሲመ​ለሱ፥ ኀያ​ላ​ኖ​ቻ​ቸ​ውም ሲደ​ክሙ፥ ወደ ኋላ​ቸ​ውም ሳይ​መ​ለ​ከቱ ፈጥ​ነው ሲሸሹ ለምን አየሁ? በዙ​ሪ​ያ​ቸ​ውም ይከ​ቡ​አ​ቸ​ዋል፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ ሕዝብ ከሰ​ሜን ሀገር ይመ​ጣል፤ ታላቅ ሕዝ​ብም ከም​ድር ዳርቻ ይነ​ሣል።


የሕ​ዝቤ ልጅ ሆይ፥ ማቅ ልበሺ፤ በራ​ስ​ሺም ላይ አመድ ነስ​ንሺ፥ አጥፊ በላ​ያ​ችን በድ​ን​ገት ይመ​ጣ​ብ​ና​ልና ለተ​ወ​ዳጅ ልጅ እን​ደ​ሚ​ደ​ረግ ልቅሶ መራራ ልቅሶ አል​ቅሺ።


የፈ​ረ​ሶ​ቹን የሩጫ ድምፅ ከዳን ሰማን፤ ከሠ​ራ​ዊቱ ፈረ​ሶች ሩጫ ድምፅ የተ​ነ​ሣም ምድር በመ​ላዋ ተን​ቀ​ጠ​ቀ​ጠች፤ መጥ​ተ​ውም ምድ​ሪ​ቱ​ንና በእ​ር​ስ​ዋም ያለ​ውን ሁሉ፥ ከተ​ማ​ዪ​ቱ​ንና የተ​ቀ​መ​ጡ​ባ​ት​ንም በሉ።


እነሆ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጽ​ዮን የለ​ምን? ወይስ ንጉ​ሥዋ በእ​ር​ስዋ ዘንድ የለ​ምን? የሚል የወ​ገኔ ሴት ልጅ ጩኸት ድምፅ ከሩቅ ሀገር ተሰማ። በተ​ቀ​ረፁ ምስ​ሎ​ቻ​ቸ​ውና በባ​ዕድ ከን​ቱ​ነ​ትስ ያስ​ቈ​ጡኝ ስለ ምን​ድን ነው?


ምድ​ርን ትተ​ና​ልና፥ ቤቶ​ቻ​ች​ን​ንም ጥለን ሄደ​ና​ልና እን​ዴት ጐሰ​ቈ​ልን! እን​ዴት አፈ​ርን! የሚል የል​ቅሶ ድምፅ በጽ​ዮን ተሰ​ም​ቶ​አል።


ዓመት በዓ​ላ​ች​ሁ​ንም ወደ ልቅሶ፥ ዝማ​ሬ​ያ​ች​ሁ​ንም ወደ ዋይታ እለ​ው​ጣ​ለሁ፤ ማቅ​ንም በወ​ገብ ሁሉ ላይ፥ ቡሃ​ነ​ት​ንም በራስ ሁሉ ላይ ላይ አመ​ጣ​ለሁ፤ እንደ ወዳጅ ልቅሶ አደ​ር​ጋ​ች​ኋ​ለሁ፤ ከእ​ር​ሱም ጋር ያሉት እንደ መከራ ቀን ይሆ​ናሉ።


በነገሥታት ላይ ያላግጣሉ፥ መሳፍንትም ዋዛ ሆነውላቸዋል፣ በምሽጉ ሁሉ ይስቃሉ፥ አፈሩንም ከምረው ይወስዱታል።


እነሆ፥ የእነርሱ ያልሆነውን መኖሪያ ይወርሱ ዘንድ በምድር ስፋት ላይ የሚሄዱትን መራሮችንና ፈጣኖችን ሕዝብ ከለዳውያንን አስነሣለሁ።