የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ኤርምያስ 19:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እኔም ያላ​ዘ​ዝ​ሁ​ትን፥ ያል​ተ​ና​ገ​ር​ሁ​ት​ንም፥ ወደ ልቤም ያል​ገ​ባ​ውን የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት አድ​ር​ገው ለበ​ዓል ልጆ​ቻ​ቸ​ውን በእ​ሳት ያቃ​ጥሉ ዘንድ የበ​ዓ​ልን የኮ​ረ​ብ​ታ​ውን መስ​ገ​ጃ​ዎች ሠር​ተ​ዋ​ልና፤

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እኔም ያላዘዝኋቸውን፣ ያልተናገርኋቸውን፣ ፈጽሞም ያላሰብሁትን፣ ወንዶች ልጆቻቸውን በእሳት ሊሠዉለት ለበኣል መስገጃ ኰረብቶች ሠርተዋል።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እኔም ያላዘዝሁትን ያልተናገርሁትንም ወደ ልቤም ያልገባውን፥ የሚቃጠለውን መሥዋዕት አድርገው ለበዓል ልጆቻቸውን በእሳት ለማቃጠል የበዓልን የኮረብታውን መስገጃዎች ሠርተዋልና

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ልጆቻቸውንም መሥዋዕት አድርገው በእሳት ለማቃጠል ለባዓል መሠዊያዎችን ሠርተዋል፤ ይህን እንዲያደርጉ አላዘዝኳቸውም፤ ከቶም ስለዚህ ነገር አላሰብኩም።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እኔም ያላዘዝሁትን ያልተናገርሁትንም ወደ ልቤም ያልገባውን፥ የሚቃጠለውን መሥዋዕት አድርገው ለበኣል ልጆቻቸውን በእሳት ያቃጥሉ ዘንድ የበኣልን የኮረብታውን መስገጃዎች ሠርተዋልና ስለዚህ፥

ምዕራፉን ተመልከት



ኤርምያስ 19:5
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም በእ​ሳት ሥዉ​አ​ቸው፤ ምዋ​ር​ተ​ኞ​ችና አስ​ማ​ተ​ኞ​ችም ሆኑ፤ ያስ​ቈ​ጡ​ትም ዘንድ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ ነገር ለማ​ድ​ረግ ራሳ​ቸ​ውን ሸጡ።


ልጁ​ንም በእ​ሳት ሠዋ፤ ሞራ ገላ​ጭም ሆነ፤ አስ​ማ​ትም አደ​ረገ፤ መና​ፍ​ስት ጠሪ​ዎ​ች​ንና ጠን​ቋ​ዮ​ች​ንም ሰበ​ሰበ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት እጅግ ክፉ ነገር አደ​ረገ፤ ኣስ​ቈ​ጣ​ውም።


ደግ​ሞም በሄ​ኖም ልጅ ሸለቆ ውስጥ ለም​ስሉ ሠዋ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት እን​ዳ​ሳ​ደ​ዳ​ቸው እንደ አሕ​ዛ​ብም ክፉ ልማድ ልጆ​ቹን በእ​ሳት አቃ​ጠለ።


ይሁ​ዳን ወደ ኀጢ​አት እን​ዲ​ያ​ገ​ቡት፥ ይህን ርኵ​ሰት ያደ​ርጉ ዘንድ፥ እኔ ያላ​ዘ​ዝ​ሁ​ት​ንና በልቤ ያላ​ሰ​ብ​ሁ​ትን ነገር፥ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ውን ለሞ​ሎክ በእ​ሳት ያሳ​ልፉ ዘንድ በሄ​ኖም ልጅ ሸለቆ ውስጥ ያሉ​ትን መሠ​ዊ​ያ​ዎች ለበ​ዓል ሠሩ።”


ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ወር​ቄን በት​ነ​ሻ​ልና ከኀ​ጢ​አት ምኞት በሠ​ራ​ሽው ዝሙት ኀፍ​ረተ ሥጋ​ሽን ገል​ጠ​ሻ​ልና በሰ​ጠ​ሻ​ቸ​ውም በል​ጆ​ችሽ ደም፥


እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ እን​ዲ​ያ​ውቁ አጠ​ፋ​ቸው ዘንድ ማኅ​ፀን የሚ​ከ​ፍ​ተ​ውን ሁሉ በአ​መ​ጡ​ልኝ ጊዜ፥ በመ​ባ​ቸው አረ​ከ​ስ​ኋ​ቸው።


ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “በዚያ ቀን ነገር ወደ ልብህ ይገ​ባል፥ ክፉ አሳ​ብ​ንም ታስ​ባ​ለህ፤ እን​ዲ​ህም ትላ​ለህ፦


ከዘ​ር​ህም ለሞ​ሎክ አት​ስጥ የአ​ም​ላ​ክ​ህ​ንም ስም አታ​ር​ክስ፤ እኔ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ።


በነ​ጋ​ውም ባላቅ በለ​ዓ​ምን ይዞ ወደ በአል ኮረ​ብታ አወ​ጣው፤ በዚ​ያም ሆኖ የሕ​ዝ​ቡን አንድ ወገን አሳ​የው።


ለአ​ም​ላ​ክህ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲሁ አታ​ድ​ርግ፤ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ቻ​ቸ​ውን ለአ​ም​ላ​ኮ​ቻ​ቸው በእ​ሳት ስለ​ሚ​ያ​ቃ​ጥሉ አሕ​ዛብ ለአ​ም​ላ​ኮ​ቻ​ቸው የሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​ትን ርኩስ ነገር እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይጠ​ላ​ልና።