ያዕቆብ 5:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወንድሞች ሆይ! ከእናንተ ማንም ከእውነት ቢስት አንዱም ቢመልሰው፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወንድሞቼ ሆይ፤ ከእናንተ አንዱ ከእውነት ቢስትና ሌላው ቢመልሰው፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወንድሞቼ ሆይ! ከእናንተ አንዱ ከእውነት ቢስትና ሌላው ቢመልሰው፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወንድሞቼ ሆይ! ከእናንተ አንዱ ከእውነት መንገድ ቢወጣና ሌላው ወደ እውነት መንገድ ቢመልሰው መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወንድሞች ሆይ፥ ከእናንተ ማንም ከእውነት ቢስት አንዱም ቢመልሰው፥ |
ሕዝቤ ሆይ፥ ገዥዎቻችሁ ያስጨንቁአችኋል፤ አስጨናቂዎች ሴቶችም በላያችሁ ይሠለጥኑባችኋል። ሕዝቤ ሆይ፥ የሚያመሰግኑአችሁ ያስቱአችኋል፤ የምትሄዱበትንም መንገድ ያጠፋሉ።
የጠፋውንም እፈልጋለሁ፤ የባዘነውንም እመልሳለሁ፤ የተሰበረውንም እጠግናለሁ፤ የደከመውንም አጸናለሁ፤ የወፈረውንና የበረታውንም እጠብቃለሁ፤ በፍርድም እጠብቃቸዋለሁ።”
የደከመውን አላጸናችሁትም፤ የታመመውንም አልፈወሳችሁትም፤ የተሰበረውንም አልጠገናችሁትም፤ የባዘነውንም አልመለሳችሁትም፤ የጠፋውንም አልፈለጋችሁትም፤ በኀይልና በጭቈናም ገዛችኋቸው።
ወንድሞቻችን ሆይ፥ ከእናንተ ወገን የተሳሳተ ሰው ቢኖር በመንፈስ ቅዱስ የጸናችሁ እናንት እንዳትሳሳቱ ለራሳችሁ እየተጠበቃችሁ፥ እንደዚህ ያለውን ሰው ቅንነት ባለው ልቡና አጽኑት።