የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ሆሴዕ 5:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የሚ​ያ​ድኑ አዳ​ኞች ያጠ​ም​ዱ​ባት ዘንድ ተከ​ሏት፤ እኔ ግን መካ​ሪ​ያ​ችሁ ነኝ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ዐመፀኞች በግድያ በርትተዋል፤ ሁሉንም እቀጣቸዋለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ዓመፀኞችም እርድ አብዝተዋል፤ እኔ ግን እነርሱን ሁሉ እገሥጻለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ዐመፀኞች የግድያ ሥራቸውን አስፋፍተዋል፤ ስለዚህ ሁሉንም እቀጣቸዋለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ዓመፀኞችም እርድ አብዝተዋል፥ እኔ ግን እነዚያን ሁሉ እዘልፋለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት



ሆሴዕ 5:2
18 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እን​ግ​ዲህ በበ​ደል ላይ በደል እየ​ጨ​መ​ራ​ችሁ ለምን ትቀ​ሠ​ፋ​ላ​ችሁ? ራስ ሁሉ ለሕ​ማም፥ ልብም ሁሉ ለኀ​ዘን ሆኖ​አል።


ምክ​ራ​ቸ​ውን ጥልቅ አድ​ር​ገው ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሚ​ሰ​ውሩ ወዮ​ላ​ቸው! ሥራ​ቸ​ው​ንም በጨ​ለማ ውስጥ አድ​ር​ገው፥ “ማን ያየ​ናል? ወይስ ማን ያው​ቀ​ናል?” ለሚሉ ወዮ​ላ​ቸው!


እነ​ር​ሱም፥ “ሕግ ከካ​ህን፥ ምክ​ርም ከጠ​ቢብ፥ ቃልም ከነ​ቢይ አይ​ጠ​ፋ​ምና ኑ፤ በኤ​ር​ም​ያስ ላይ ምክ​ርን እን​ም​ከር። ኑ፤ በም​ላስ እን​ም​ታው፤ ቃሉ​ንም ሁሉ አና​ዳ​ምጥ” አሉ።


አቤቱ! ዐይ​ኖ​ችህ ለሃ​ይ​ማ​ኖት አይ​ደ​ሉ​ምን? አንተ ቀሥ​ፈ​ሃ​ቸ​ዋል፤ ነገር ግን አላ​ዘ​ኑም፤ ቀጥ​ቅ​ጠ​ሃ​ቸ​ው​ማል፤ ነገር ግን ተግ​ሣ​ጽን እንቢ አሉ፤ ፊታ​ቸ​ውን ከድ​ን​ጋይ ይልቅ አጠ​ን​ክ​ረ​ዋል፤ ይመ​ለ​ሱም ዘንድ እንቢ አሉ።


እነ​ርሱ ሁሉ እጅግ ደን​ቆ​ሮ​ዎች ናቸው፤ በጠ​ማ​ማ​ነት ይሄ​ዳሉ፤ ሁሉም እንደ ናስና ብረት የዛጉ ናቸው።


ነገር ግን ሐሰት፥ ግዳ​ይና ስር​ቆት፥ ምን​ዝ​ር​ናም ምድ​ርን ሞል​ተ​ዋል፤ ደም​ንም ከደም ጋር ይቀ​ላ​ቅ​ላሉ።


ስለ​ዚህ ነቢ​ያ​ቶ​ቻ​ች​ሁን አጨ​ድ​ኋ​ቸው፤ በአ​ፌም ቃል ገደ​ል​ኋ​ቸው፤ ፍር​ዴም እንደ ብር​ሃን ይወ​ጣል።


ሰውን እን​ደ​ሚ​ያ​ደቡ ወን​በ​ዴ​ዎች፥ እን​ዲሁ ካህ​ናት በሴ​ኬም መን​ገድ ላይ አድ​ብ​ተው ይገ​ድ​ላሉ፤ ዐመ​ፅ​ንም ያደ​ር​ጋሉ።


ክፋ​ታ​ቸ​ውም ሁሉ በጌ​ል​ገላ አለ፤ በዚያ ጠል​ቻ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ስለ ሠሩት ክፋት ከቤቴ አሳ​ድ​ዳ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲያ አል​ወ​ድ​ዳ​ቸ​ውም፤ አለ​ቆ​ቻ​ቸው ሁሉ ዐመ​ፀ​ኞች ናቸ​ውና።


እኔ የምወዳቸውን ሁሉ እገሥጻቸዋለሁ፤ እቀጣቸውማለሁ፤ እንግዲህ ቅና፤ ንስሓም ግባ።