የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዘፍጥረት 34:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ኤሞ​ርም እን​ዲህ ብሎ ነገ​ራ​ቸው፥ “ልጄ ሴኬም ልጃ​ች​ሁን ወዶ​አ​ታ​ልና ሚስት እን​ድ​ት​ሆ​ነው እር​ስ​ዋን ስጡት።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ኤሞር ግን እንዲህ አላቸው፤ “ልጄ ሴኬም ልቡ በልጃችሁ ፍቅር ተነድፏል፤ እባካችሁ እንዲያገባት ፍቀዱለት።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሐሞርም እንዲህ ብሎ ነገራቸው፥ “ልጄ ሴኬም በልጃችሁ ፍቅር ነፍሱ ተወስዳለችና ሚስት እንድትሆነው እባካችሁ እርሷን ስጡት።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሐሞር ግን እንዲህ አላቸው፤ “ልጄ ሴኬም ልጃችሁን በጣም ወዶአታል፤ ስለዚህ እንዲያገባት ፍቀዱለት፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ኤሞርም እንዲህ ብሎ ነገራቸው፦ ልጄ ሴኬም በልጃችሁ ፍቅር ልቡ ተነድፎአልና ሚስት እንድትሆነው እባካችሁ እርስዋን ስጡት።

ምዕራፉን ተመልከት



ዘፍጥረት 34:8
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ልቡ​ና​ውም በያ​ዕ​ቆብ ልጅ በዲና ፍቅር ተነ​ደፈ፤ ብላ​ቴ​ና​ዪ​ቱ​ንም ወደ​ዳት፤ ልብ​ዋ​ንም ደስ በሚ​ያ​ሰ​ኛት ነገር ተና​ገ​ራት።


የያ​ዕ​ቆ​ብም ልጆች ከም​ድረ በዳ መጡ፤ ይህ​ንም በሰሙ ጊዜ ፈጽ​መው ደነ​ገጡ፤ የያ​ዕ​ቆ​ብን ልጅ በመ​ተ​ኛቱ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ኀፍ​ረ​ትን ስላ​ደ​ረገ አዘኑ፤ እጅ​ግም ተቈጡ፤ እን​ዲህ አይ​ደ​ረ​ግ​ምና።


ጋብ​ቾ​ችም ሁኑን፤ ሴቶች ልጆ​ቻ​ች​ሁን ስጡን፤ እና​ን​ተም የእ​ኛን ሴቶች ልጆች ለል​ጆ​ቻ​ችሁ ውሰዱ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች፥ “አም​ላ​ኮ​ቻ​ቸ​ውን ትከ​ተሉ ዘንድ ልባ​ች​ሁን እን​ዳ​ይ​መ​ልሱ ወደ እነ​ርሱ አት​ግቡ፥ እነ​ር​ሱም ወደ እና​ንተ አይ​ግቡ” ካላ​ቸው ከአ​ሕ​ዝብ አገባ፤ ሰሎ​ሞን ግን እነ​ር​ሱን ተከ​ተለ፤ ወደ​ዳ​ቸ​ውም።


ወይም ጌታ​ውን እን​ደ​ሚ​ፈራ አገ​ል​ጋይ ጥላ​ው​ንም እን​ደ​ሚ​መኝ፥ ወይም ደመ​ወ​ዙን እን​ደ​ሚ​ጠ​ብቅ ምን​ደኛ አይ​ደ​ለ​ምን?


አቤቱ፥ ወደ አንተ የለ​መ​ን​ሁ​ትን ጸሎ​ቴን ስማኝ፥ ከጠ​ላ​ትም ጥር​ጥር ነፍ​ሴን አድ​ናት።


የሕ​ዝ​ብ​ህን ኀጢ​አት ይቅር አልህ፤ ዐበ​ሳ​ቸ​ው​ንም ሁሉ ሰወ​ርህ።


ነፍ​ሳ​ች​ሁም ወደ​ም​ት​መ​ኛት ወደ​ዚ​ያች ምድር አት​መ​ለ​ሱም።