የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዘፍጥረት 25:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

አብ​ር​ሃ​ምም የኖ​ረ​በት የዕ​ድ​ሜው ዓመ​ታት እነ​ዚህ ናቸው፤ መቶ ሰባ አም​ስት ዓመት ኖረ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

አብርሃም በጠቅላላው መቶ ሰባ ዐምስት ዓመት ኖረ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

አብርሃምም በሕይወት የኖረበት የዕድሜው ዘመን መቶ ሰባ አምስት ዓመታት ናቸው።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የአብርሃም ዕድሜ በአጠቃላይ መቶ ሰባ አምስት ዓመት ነበር፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

አብርሃምም የኖረበት የዕድሜው ዓመታት እነዚህ ናቸው መቶ ሰባ አምስት ዓመት ኖረ።

ምዕራፉን ተመልከት



ዘፍጥረት 25:7
6 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አብ​ራ​ምም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ነገ​ረው ሄደ፤ ሎጥም ከእ​ርሱ ጋር ሄደ፤ አብ​ራ​ምም ከካ​ራን በወጣ ጊዜ ሰባ አም​ስት ዓመት ሆኖት ነበረ።


የይ​ስ​ሐ​ቅም ዕድሜ መቶ ሰማ​ንያ ዓመት ሆነ።


ይስ​ሐ​ቅም ሸም​ግሎ ዕድ​ሜ​ንም ጠግቦ ሞተ፤ ወደ ወገ​ኖ​ቹም ተጨ​መረ፤ ልጆ​ቹም ዔሳ​ውና ያዕ​ቆብ ቀበ​ሩት።


ያዕ​ቆ​ብም በግ​ብፅ ምድር ዐሥራ ሰባት ዓመት ተቀ​መጠ፤ የያ​ዕ​ቆ​ብም መላው የሕ​ይ​ወቱ ዘመን መቶ አርባ ሰባት ዓመት ሆነ።


ያዕ​ቆ​ብም ለፈ​ር​ዖን አለው፥ “በእ​ን​ግ​ድ​ነት የኖ​ር​ሁት የሕ​ይ​ወቴ ዘመ​ንስ መቶ ሠላሳ ዓመት ነው፤ የሕ​ይ​ወ​ቴም ዘመ​ኖች ጥቂ​ትም ክፉም ሆኑ​ብኝ፤ አባ​ቶች በእ​ን​ግ​ድ​ነት የተ​ቀ​መ​ጡ​በ​ት​ንም ዘመን አያ​ህ​ሉም።”


ዮሴ​ፍም በመቶ ዐሥር ዓመት ዕድ​ሜው ሞተ፤ በሽ​ቱም አሹት፤ በግ​ብፅ ምድ​ርም በሣ​ጥን ውስጥ አኖ​ሩት።