የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዘፀአት 7:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ያዘ​ዝ​ሁ​ህን ነገር ሁሉ አንተ ትነ​ግ​ረ​ዋ​ለህ፤ ወን​ድ​ም​ህም አሮን የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ከሀ​ገሩ ይለ​ቅቅ ዘንድ ለፈ​ር​ዖን ይን​ገ​ረው።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እኔ የማዝህን ሁሉ ትናገራለህ፤ ወንድምህ አሮንም እስራኤላውያንን ከአገሩ እንዲወጡ ይለቅቃቸው ዘንድ ለፈርዖን ይነግረዋል።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

አንተ ያዘዝሁህን ሁሉ ትነግረዋለህ፤ ወንድምህም አሮን የእስራኤልን ልጆች ከአገሩ እንዲለቅ ፈርዖንን ይነግረዋል።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እኔ የማዝህን ሁሉ ለአሮን ንገረው፤ እርሱም ከአገሩ እንዲወጡ እስራኤላውያንን ይለቅ ዘንድ ለንጉሡ ይነግረዋል፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ያዘዝሁህን ነገር ሁሉ አንተ ትነግረዋለህ፤ ወንድምህም አሮን የእስራኤልን ልጆች ከአገሩ ይለቅቅ ዘንድ ከፈርዖን ጋር ይናገራል።

ምዕራፉን ተመልከት



ዘፀአት 7:2
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሚክ​ያ​ስም፥ “ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ነ​ግ​ረ​ኝን እር​ሱን እና​ገ​ራ​ለሁ” አለ።


አን​ተም ትና​ገ​ረ​ዋ​ለህ፤ ቃሌ​ንም በአፉ ታደ​ር​ገ​ዋ​ለህ፤ እኔ አን​ደ​በ​ት​ህ​ንና አን​ደ​በ​ቱን አረ​ታ​ለሁ፤ የም​ታ​ደ​ር​ጉ​ት​ንም አለ​ብ​ማ​ች​ኋ​ለሁ።


እርሱ ስለ አንተ ከሕ​ዝቡ ጋር ይነ​ጋ​ገ​ራል፤ እርሱ አፍ ይሆ​ን​ል​ሃል፤ አን​ተም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ትሆ​ን​ለ​ታ​ለህ።


ከዚ​ህም በኋላ ሙሴና አሮን ወደ ፈር​ዖን ገብ​ተው እን​ዲህ አሉት፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ‘በም​ድረ በዳ በዓል ያደ​ር​ግ​ልኝ ዘንድ ሕዝ​ቤን ልቀቅ።’ ”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን፥ “እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ፤ እኔ የም​ነ​ግ​ር​ህን ሁሉ ለግ​ብፅ ንጉሥ ለፈ​ር​ዖን ንገር” ብሎ ተና​ገ​ረው።


ሙሴና አሮ​ንም እን​ዲህ አደ​ረጉ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ዘ​ዛ​ቸው አደ​ረጉ።


አንተ ግን ወገ​ብ​ህን ታጠቅ፤ ተነ​ሥም፤ ያዘ​ዝ​ሁ​ህ​ንም ሁሉ ንገ​ራ​ቸው፤ ከፊ​ታ​ቸ​ውም የተ​ነሣ አት​ፍራ። በፊ​ታ​ቸ​ውም አት​ደ​ን​ግጥ አድ​ንህ ዘንድ እኔ ከአ​ንተ ጋር ነኝና ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን እን​ዲህ አለኝ፥ “ወደ​ም​ል​ክህ ሁሉ ዘንድ ትሄ​ዳ​ለ​ህና፥ የማ​ዝ​ዝ​ህ​ንም ሁሉ ትና​ገ​ራ​ለ​ህና፦ ሕፃን ነኝ አት​በል።


እር​ሱም፥ “የሰው ልጅ ሆይ! የነ​ገ​ር​ሁ​ህን ቃሌን ሁሉ በል​ብህ ጠብ​ቀው፤ በጆ​ሮ​ህም ስማው።


“የሰው ልጅ ሆይ! ለእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ጕበኛ አድ​ር​ጌ​ሃ​ለሁ፤ ስለ​ዚህ የአ​ፌን ቃል ስማ፤ በቃ​ሌም ገሥ​ጻ​ቸው።


ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምክር ሁሉ የሰ​ወ​ር​ኋ​ች​ሁና ያል​ነ​ገ​ር​ኋ​ችሁ የለም።


ዛሬ እኔ ያዘ​ዝ​ኋ​ች​ሁን የአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ ትጠ​ብ​ቃ​ላ​ችሁ እንጂ ባዘ​ዝ​ኋ​ችሁ ቃል ላይ አት​ጨ​ም​ሩም፤ ከእ​ር​ሱም አታ​ጐ​ድ​ሉም።