ስለዚህ ከሐሰት አማልክት ይልቅ በኀይሉ የሚመካ ንጉሥ፥ ወይም በቤት ውስጥ የሚጠቅም፥ የገዛውም የሚገለገልበት ሸክላ ይሻላል፤ ወይም በቤት ውስጥ ያለውን ሁሉ የሚያድን መዝጊያ ከሐሰት አማልክት ይልቅ ይሻላል፤ በነገሥታት አዳራሽ ውስጥ ያሉ የእንጨት ምሰሶዎችም ከሐሰት አማልክት ይልቅ ይሻላሉ።