የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዘዳግም 32:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የዱ​ሮ​ውን ዘመን አስብ፤ የልጅ ልጅ​ንም ዓመ​ታት አስ​ተ​ውል፤ አባ​ት​ህን ጠይቅ፥ ይነ​ግ​ር​ህ​ማል፤ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ች​ህን ጠይቅ፤ ይተ​ር​ኩ​ል​ህ​ማል።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የጥንቱን ዘመን አስታውስ፤ አባትህን ጠይቅ፤ ይነግርሃልም፤ ሽማግሌዎችህንም ጠይቅ፤ ያስረዱሃል።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

“የቀድሞውን ዘመን አስታውስ፤ የብዙ ትውልድንም ዓመታት አስተውል፥ አባትህን ጠይቅ፥ እርሱም ያስታውቅሃል፥ ሽማግሌዎችህን ጠይቅ፥ እነርሱም ይነግሩሃል።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

“የቀድሞውን ዘመን አስታውስ፤ ከዘመናት በፊት የነበረውን አስተውል፤ አባትህን ጠይቅ እርሱም ይነግርሃል፤ ሽማግሌዎችህን ጠይቅ እነርሱም ይተርኩልሃል።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የዱሮውን ዘመን አስብ፥ 2 የብዙ ትውልድንም ዓመታት አስተውል፤ 2 አባትህን ጠይቅ፥ ያስታውቅህማል፤ 2 ሽማግሌዎችህን ጠይቅ፥ ይነግሩህማል። 2

ምዕራፉን ተመልከት



ዘዳግም 32:7
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ወጥ​መድ በኃ​ጥ​ኣን ላይ ይዘ​ን​ባል፤ እሳ​ትና ዲን፥ ዐውሎ ነፋ​ስም የጽ​ዋ​ቸው እድል ፋንታ ነው።


ልቤ መል​ካም ነገ​ርን ተና​ገረ፥ እኔም ሥራ​ዬን ለን​ጉሥ እና​ገ​ራ​ለሁ፤ አን​ደ​በቴ እንደ ፈጣን ጸሓፊ ብርዕ ነው።


ውበቱ ከሰው ልጆች ይልቅ ያም​ራል፤ ሞገስ ከከ​ን​ፈ​ሮ​ችህ ፈሰሰ፤ ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለዘ​ለ​ዓ​ለም ባረ​ከህ።


እንደ አባ​ቶ​ቻ​ቸው እን​ዳ​ይ​ሆኑ፥ ጠማ​ማና የም​ታ​ስ​መ​ርር ትው​ልድ፥ ልብ​ዋን ያላ​ቀ​ናች ትው​ልድ፥ መን​ፈ​ስዋ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ያል​ታ​መ​ነች።


አቤቱ፥ እስከ መቼ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ትቈ​ጣ​ለህ? ቅን​ዐ​ት​ህም እንደ እሳት ይነ​ድ​ዳል?


ልጆ​ቻ​ችሁ፦ ‘ይህ ሥር​ዐት ለእ​ና​ንተ ምን​ድር ነው?’ ባሉ​አ​ችሁ ጊዜ እና​ንተ፦


እን​ዲ​ህም ይሆ​ናል፤ ከዚህ በኋላ ልጅህ፦ ‘ይህ ምን​ድን ነው?’ ብሎ በጠ​የ​ቀህ ጊዜ እን​ዲህ ትለ​ዋ​ለህ፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በብ​ርቱ እጅ ከባ​ር​ነት ቤት ከግ​ብፅ ምድር አወ​ጣን፤


እኔ አም​ላክ ነኝና፤ ያለ እኔም ሌላ የለ​ምና የቀ​ድ​ሞ​ው​ንና የጥ​ን​ቱን ነገር ዐስቡ። እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ፤ እንደ እኔም ያለ ማንም የለም።


እር​ሱም እን​ዲህ ብሎ የቀ​ደ​መ​ውን ዘመን ዐሰበ፥ “በበ​ጎቹ እረኛ እጅ ከግ​ብፅ በወጡ ጊዜ መል​አ​ኬን በፊ​ታ​ቸው ላክሁ።


“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰውን በም​ድር ላይ ከፈ​ጠ​ረው ጀምሮ፥ ከሰ​ማይ ዳር እስከ ሰማይ ዳርቻ ድረስ ከቶ እን​ዲህ ያለ ታላቅ ነገር ሆኖ፥ ወይም እንደ እርሱ ያለ ተሰ​ምቶ እንደ ሆነ ከአ​ንተ በፊት የነ​በ​ረ​ውን የቀ​ደ​መ​ውን ዘመን ጠይቅ።


አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይፈ​ት​ንህ ዘንድ፥ በል​ብ​ህም ያለ​ውን ትእ​ዛ​ዙን ትጠ​ብቅ ወይም አት​ጠ​ብቅ እንደ ሆነ ያውቅ ዘንድ፥ ሊያ​ስ​ጨ​ን​ቅህ በም​ድረ በዳ የመ​ራ​ህን መን​ገድ ሁሉ አስብ።


ጌዴ​ዎ​ንም፥ “ጌታዬ ሆይ! እሺ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ይህ ነገር ሁሉ ለምን ደረ​ሰ​ብን? አባ​ቶ​ቻ​ች​ንስ፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከግ​ብፅ አው​ጥ​ቶ​ናል ብለው ይነ​ግ​ሩን የነ​በረ ተአ​ም​ራት ወዴት አለ? አሁን ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትቶ​ናል፤ በም​ድ​ያም እጅም አሳ​ልፎ ሰጥ​ቶ​ናል” አለው።