የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዘዳግም 32:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እን​ዲ​ህም አለ፦ “ሰማይ ሆይ፥ አድ​ምጥ፥ ልን​ገ​ርህ፤ ምድ​ርም የአ​ፌን ቃሎች ትስማ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሰማያት ሆይ፤ አድምጡ፤ እኔም እናገራለሁ፤ ምድር ሆይ፤ አንቺም የአፌን ቃል ስሚ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

“ሰማያት ሆይ፥ አድምጡ፥ እኔም እናገራለሁ፤ ምድርም የአፌን ቃሎች ትስማ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሰማይ ሆይ፥ የምናገረውን አድምጥ፤ ምድርም ከአፌ የሚወጣውን ቃል ትስማ፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሰማያት ሆይ፥ አድምጡ፥ እኔም እናገራለሁ፤ 2 ምድርም የአፌን ቃሎች ትስማ።

ምዕራፉን ተመልከት



ዘዳግም 32:1
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የአ​ማ​ል​ክት አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተና​ገረ፥ ምድ​ር​ንም ጠራት፤ ከፀ​ሐይ መውጫ ጀምሮ እስከ መግ​ቢ​ያዋ ድረስ።


አን​ተን ብቻ በደ​ልሁ፥ በፊ​ት​ህም ክፋ​ትን አደ​ረ​ግሁ፥ በነ​ገ​ርህ ትጸ​ድቅ ዘንድ በፍ​ር​ድ​ህም ታሸ​ንፍ ዘንድ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ብሎ ተና​ግ​ሮ​አ​ልና፥ “ሰማይ ስማ፤ ምድ​ርም አድ​ምጪ፤ ልጆ​ችን ወለ​ድሁ፤ አሳ​ደ​ግ​ሁም፤ እነ​ር​ሱም ዐመ​ፁ​ብኝ።


እና​ንተ አሕ​ዛብ ሆይ፥ ቅረቡ፤ እና​ን​ተም አለ​ቆች ሆይ፥ አድ​ምጡ፤ ምድ​ርና በው​ስ​ጥ​ዋም ያሉ፥ ዓለ​ምና በው​ስ​ጥ​ዋም ያሉ ሕዝብ ሁሉ ይስሙ።


ሰማይ በዚህ ደነ​ገጠ፤ እጅ​ግም ተን​ቀ​ጠ​ቀጠ” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ምድር ሆይ! ምድር ሆይ! ምድር ሆይ! የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሚ።


ምድር ሆይ፥ ስሚ! እነሆ ቃሌን ስላ​ል​ሰሙ፥ ሕጌ​ንም ስለ ጣሉ፥ እኔ​ንም ስለ ናቁ በዚህ ሕዝብ ላይ እንደ ሥራ​ቸው ፍሬ፥ ክፉን ነገር አመ​ጣ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ።


በፊ​ትህ ሕይ​ወ​ት​ንና ሞትን፥ በረ​ከ​ት​ንና መር​ገ​ምን እን​ዳ​ስ​ቀ​መ​ጥሁ እኔ ዛሬ ሰማ​ይ​ንና ምድ​ርን በአ​ንተ ላይ አስ​መ​ሰ​ክ​ራ​ለሁ፤ እን​ግ​ዲህ አን​ተና ዘርህ በሕ​ይ​ወት ትኖሩ ዘንድ ሕይ​ወ​ትን ምረጥ፤


አሁ​ንም ይህ​ችን መዝ​ሙር ለእ​ና​ንተ ጻፉ፤ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች አስ​ተ​ም​ሩ​አ​ቸው፤ ይህ​ችም መዝ​ሙር በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ምስ​ክር ትሆ​ን​ልኝ ዘንድ በአ​ፋ​ቸው አድ​ር​ጓት።


ይህን ቃል በጆ​ሮ​አ​ቸው እነ​ግር ዘንድ፥ ሰማ​ይ​ንና ምድ​ር​ንም አስ​መ​ሰ​ክ​ር​ባ​ቸው ዘንድ የነ​ገ​ዶ​ቻ​ች​ሁን አለ​ቆች፥ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ቻ​ች​ሁን ሁሉ፥ ሹሞ​ቻ​ች​ሁ​ንም፥ ጻፎ​ቻ​ች​ሁ​ንም ሰብ​ስ​ቡ​ልኝ፤


ሙሴም በእ​ስ​ራ​ኤል ጉባኤ ሁሉ ጆሮ የዚ​ህ​ችን መዝ​ሙር ቃሎች እስከ መጨ​ረ​ሻው ድረስ ተና​ገረ።


ትወ​ር​ሱ​አት ዘንድ ዮር​ዳ​ኖ​ስን ተሻ​ግ​ራ​ችሁ ከም​ት​ገ​ቡ​ባት ምድር ፈጥ​ና​ችሁ እን​ድ​ት​ጠፉ እኔ ዛሬ ሰማ​ይ​ንና ምድ​ርን በእ​ና​ንተ አስ​መ​ሰ​ክ​ራ​ለሁ፤ ፈጽ​ሞም ትጠ​ፋ​ላ​ችሁ እንጂ ረዥም ዘመን አት​ቀ​መ​ጡ​ባ​ትም።