የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዘዳግም 26:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ግብ​ፃ​ው​ያ​ንም ክፉ ነገር አደ​ረ​ጉ​ብን፤ አስ​ጨ​ነ​ቁ​ንም፤ በላ​ያ​ች​ንም ከባድ ሥራን ጫኑ​ብን፤

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ግብጻውያን ግን ከባድ ሥራ በማሠራት አንገላቱን፤ አሠቃዩንም።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ግብፃውያን ግን አንገላቱን፤ አሠቃዩንም፤ በባርነት የጭካኔ ቀንበር ጫኑብን።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ግብጻውያን ግን አስጨነቁን፤ አዋረዱን፥ ባርያዎችም ሆነን እንድናገለግል አስገደዱን።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ግብፃውያንም ክፉ ነገር አደረጉብን፥ አስጨነቁንም፥ በላያችንም ጽኑ ከባድ ሥራን ጫኑብን፤

ምዕራፉን ተመልከት



ዘዳግም 26:6
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በብ​ርቱ ሥራም ያስ​ጨ​ን​ቋ​ቸው ዘንድ የሠ​ራ​ተ​ኞች አለ​ቆ​ችን ሾመ​ባ​ቸው፤ ለፈ​ር​ዖ​ንም ፌቶ​ምን፥ ራም​ሴ​ንና የፀ​ሐይ ከተማ የም​ት​ባል ዖንን ጽኑ ከተ​ሞች አድ​ር​ገው ሠሩ።


በጽኑ ሥራ፥ በጭቃ፥ በጡ​ብም፥ በእ​ር​ሻም ሥራ ሁሉ፥ በመ​ከ​ራም በሚ​ያ​ሠ​ሩ​አ​ቸው ሥራ ሁሉ፤ ሕይ​ወ​ታ​ቸ​ውን ያስ​መ​ር​ሩ​አ​ቸው ነበር።


“እና​ንተ ዕብ​ራ​ው​ያ​ትን ሴቶች ስታ​ዋ​ልዱ ለመ​ው​ለድ እንደ ደረሱ በአ​ያ​ችሁ ጊዜ፥ ወንድ ቢሆን ግደ​ሉት፤ ሴት ብት​ሆን ግን አት​ግ​ደ​ሏት።”


ፈር​ዖ​ንም፥ “የሚ​ወ​ለ​ደ​ውን ወንድ ልጅ ሁሉ ወደ ወንዝ ጣሉት፤ ሴትን ልጅ ሁሉ ግን በሕ​ይ​ወት አድ​ኑ​አት” ብሎ ሕዝ​ቡን ሁሉ አዘዘ።


በግ​ብፅ ዮሴ​ፍን ያላ​ወቀ ሌላ ንጉሥ ተነሣ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች አለ​ቆች ዕለት ዕለት ከም​ት​ሠ​ሩት ከጡቡ ቍጥር ምንም አታ​ጕ​ድሉ ባሉ​አ​ቸው ጊዜ ነገሩ እንደ ከፋ​ባ​ቸው አዩ።


በስ​ምህ እና​ገር ዘንድ ወደ ፈር​ዖን ከገ​ባሁ ወዲህ፥ ይህን ሕዝብ አስ​ከ​ፍ​ቶ​ታ​ልና፤ አን​ተም ሕዝ​ብ​ህን ከቶ አላ​ዳ​ን​ኸ​ውም” አለ።


በእ​ነ​ዚህ ሰዎች ላይ ሥራው ይክ​በ​ድ​ባ​ቸው፤ ይህን ብቻ ያስ​ባሉ፤ ከንቱ ቃልም አያ​ስ​ቡም።”


አባ​ቶ​ቻ​ችን ወደ ግብፅ ወረዱ፤ በግ​ብ​ፅም እጅግ ዘመን ተቀ​መ​ጥን፤ ግብ​ፃ​ው​ያ​ንም እኛ​ንና አባ​ቶ​ቻ​ች​ንን በደሉ።


ወደ አባ​ቶ​ቻ​ች​ንም አም​ላክ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኽን፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃላ​ች​ንን ሰማ፤ ጭን​ቀ​ታ​ች​ን​ንም፥ ድካ​ማ​ች​ን​ንም፥ ግፋ​ች​ን​ንም አየ፤


እና​ን​ተን ግን እንደ ዛሬው ሁሉ የር​ስቱ ሕዝብ ትሆ​ኑ​ለት ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወስዶ ከብ​ረት እቶን ከግ​ብፅ አወ​ጣ​ችሁ።