የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዘዳግም 17:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እር​ሱን ለመ​ግ​ደል በመ​ጀ​መ​ሪያ የም​ስ​ክ​ሮች እጅ በኋ​ላም የሕ​ዝቡ ሁሉ እጅ ትሁ​ን​በት፤ እን​ዲሁ ክፉ​ውን ከመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ አስ​ወ​ግዱ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሲገደልም መጀመሪያ የምስክሮቹ እጅ፣ ቀጥሎም የሕዝቡ ሁሉ እጅ ይረፍበት፤ ክፉን ከመካከልህ አስወግድ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሲገደልም መጀመሪያ የምስክሮቹ እጅ፥ ቀጥሎም የሕዝቡ ሁሉ እጅ ይረፍበት፤ እንዲሁም ክፋቱን ከመካከልህ አስወግድ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ምስክሮቹ የመጀመሪያዎቹን ድንጋዮች ይወርውሩ፤ ከዚያም ቀጥሎ ሌላው ሕዝብ በድንጋይ ይውገረው፤ በዚህም ዐይነት እንደዚህ ያለውን ክፉ ነገር ሁሉ ከመካከልህ ታስወግዳለህ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እርሱን ለመግደል በመጀመሪያ የምስክሮች እጅ በኋላም የሕዝቡ ሁሉ እጅ ትሁንበት፤ እንዲሁም ክፋቱን ከመካከልህ አስወግድ።

ምዕራፉን ተመልከት



ዘዳግም 17:7
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“ተሳ​ዳ​ቢ​ውን ከሰ​ፈር ወደ ውጭ አው​ጣው፤ የሰ​ሙ​ትም ሁሉ እጃ​ቸ​ውን በራሱ ላይ ይጫ​ኑ​በት፤ ማኅ​በ​ሩም ሁሉ በድ​ን​ጋይ ይው​ገ​ሩት።”


ብዙ ጊዜ መላ​ል​ሰው በጠ​የ​ቁት ጊዜም ዐይ​ኖ​ቹን አን​ሥቶ፥ “ከእ​ና​ንተ ኀጢ​ኣት የሌ​ለ​በት አስ​ቀ​ድሞ ድን​ጋይ ይጣ​ል​ባት” አላ​ቸው።


በውጭ ያሉ​ትን ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይፈ​ር​ድ​ባ​ቸ​ዋል፤ ይቀ​ጣ​ቸ​ዋ​ልም፤ ክፉ​ውን ከእ​ና​ንተ አርቁ።


ከግ​ብፅ ምድር ከባ​ር​ነት ቤት ካወ​ጣህ ከአ​ም​ላ​ክህ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሊያ​ር​ቅህ ወድ​ዶ​አ​ልና በድ​ን​ጋይ ይው​ገ​ሩት፤ ይግ​ደ​ሉ​ትም።


ከግ​ብፅ ምድር ካወ​ጣ​ችሁ፥ ከባ​ር​ነ​ትም ቤት ካዳ​ና​ችሁ ከአ​ም​ላ​ካ​ችሁ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሊያ​ስ​ታ​ችሁ፥ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ትሄ​ድ​ባት ዘንድ ካዘ​ዘህ መን​ገድ ሊያ​ወ​ጣህ ተና​ግ​ሮ​አ​ልና ያ ነቢይ ወይም ሕልም አላሚ ይገ​ደል፤ እን​ዲ​ሁም ክፉ​ውን ነገር ከአ​ንተ አርቅ።


“የአ​ባ​ትህ ወይም የእ​ና​ትህ ልጅ ወን​ድ​ምህ ወይም ወንድ ልጅህ ወይም ሴት ልጅህ ወይም አብ​ራህ የም​ት​ተኛ ሚስ​ትህ ወይም እንደ ነፍ​ስህ ያለ ወዳ​ጅህ በስ​ውር፦ ና፥ ሄደን አን​ተም አባ​ቶ​ች​ህም የማ​ታ​ው​ቋ​ቸ​ውን ሌሎች አማ​ል​ክት እና​ም​ልክ ብሎ ቢያ​ስ​ትህ፥


ነገር ግን ፈጽ​መህ ተና​ገር፤ እር​ሱን ለመ​ግ​ደል በፊት ያንተ እጅ፥ ከዚ​ያም በኋላ የሕ​ዝቡ ሁሉ እጅ በላዩ ትሁን።


ማና​ቸ​ውም ሰው ቢኰራ፥ በአ​ም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ለማ​ገ​ል​ገል የሚ​ቆ​መ​ውን ካህ​ኑን ወይም በዚያ ወራት ያለ​ውን ፈራ​ጁን ባይ​ሰማ ያ ሰው ይሙት፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ዘንድ ክፉ​ውን አስ​ወ​ግዱ፤


በወ​ን​ድሙ ላይ ክፋ​ትን ያደ​ርግ ዘንድ እንደ ወደደ በእ​ርሱ ላይ ታደ​ር​ጉ​በ​ታ​ላ​ችሁ፤ እን​ዲ​ሁም ከእ​ና​ንተ መካ​ከል ክፉ​ውን ታስ​ወ​ግ​ዳ​ላ​ችሁ።


የከ​ተ​ማ​ዉም ሰዎች ሁሉ በድ​ን​ጋይ ደብ​ድ​በው ይግ​ደ​ሉት፤ እን​ዲ​ህም ክፉ​ውን ነገር ከመ​ካ​ከ​ልህ ታር​ቃ​ለህ፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ሰም​ተው ይፈ​ራሉ።


ብላ​ቴ​ና​ዪ​ቱን ወደ አባቷ ቤት ደጅ ያው​ጡ​አት፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ዘንድ ስን​ፍ​ናን አድ​ር​ጋ​ለ​ችና፥ የአ​ባ​ቷ​ንም ቤት አስ​ነ​ው​ራ​ለ​ችና የከ​ተ​ማው ሰዎች በድ​ን​ጋይ ወግ​ረው ይግ​ደ​ሉ​አት፤ እን​ዲ​ሁም ክፉ​ውን ነገር ከመ​ካ​ከ​ልህ ታስ​ወ​ግ​ዳ​ለህ።


“ማና​ቸ​ውም ሰው ከሌላ ሰው ሚስት ጋር ተኝቶ ቢገኝ፥ አመ​ን​ዝ​ራ​ውና አመ​ን​ዝ​ራ​ዪቱ ሁለ​ታ​ቸው ይገ​ደሉ፤ እን​ዲ​ሁም ክፉ​ውን ነገር ከእ​ስ​ራ​ኤል ታስ​ወ​ግ​ዳ​ለህ።


ብላ​ቴ​ና​ዪቱ በከ​ተማ ውስጥ ሳለች አል​ጮ​ኸ​ች​ምና፥ ሰው​የ​ውም የባ​ል​ጀ​ራ​ውን ሚስት አስ​ነ​ው​ሮ​አ​ልና በድ​ን​ጋይ ወግ​ረው ይግ​ደ​ሉ​አ​ቸው፤ እን​ዲሁ ክፉ​ውን ነገር ከው​ስ​ጥህ ታስ​ወ​ግ​ዳ​ለህ።


“ማንም ሰው ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከወ​ን​ድ​ሞቹ ሰውን አፍኖ ሲሰ​ር​ቅና ሲሸጥ ቢገኝ ያን የሰ​ረ​ቀ​ውን ሰው ይግ​ደ​ሉት፤ እን​ዲ​ሁም ክፉ​ውን ነገር ከመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ አርቁ።


“አሁ​ንም በገ​ባ​ዖን ውስጥ የበ​ደሉ የዐ​መፅ ሰዎ​ችን እን​ድ​ን​ገ​ድ​ላ​ቸው አው​ጥ​ታ​ችሁ ስጡን፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ክፋ​ትን እና​ር​ቃ​ለን።” የብ​ን​ያም ልጆች ግን የወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ቸ​ውን የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ቃል ሊሰሙ አል​ወ​ደ​ዱም።