የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዘዳግም 17:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ይህን ክፉ ነገር የሠ​ሩ​ትን ያን ወንድ ወይም ያችን ሴት ታወ​ጣ​ቸ​ዋ​ለህ፥ እስ​ኪ​ሞ​ቱም ድረስ በድ​ን​ጋይ ትመ​ት​ዋ​ቸ​ዋ​ላ​ችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ይህን ክፉ ድርጊት የፈጸመውን ወንድ ወይም ሴት ወደ ከተማ ደጅ ወስደህ፣ ያን ሰው እስኪሞት ድረስ በድንጋይ ውገረው።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ይህን ክፉ ድርጊት የፈጸመውን ወንድ ወይም ሴት ወደ ከተማ ደጅ ወስደህ፥ ያን ሰው እስኪሞት ድረስ በድንጋይ ውገረው።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ያን ሰው ወይም ያቺን ሴት ከከተማ ወደ ውጪ አውጥተህ በድንጋይ ወግረህ ግደል።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ይህን ክፉ ነገር የሠሩትን ያን ወንድ ወይም ያችን ሴት ወደ በርህ ታመጣቸዋለህ፥ እስኪሞቱም ድረስ በድንጋይ ትወግራቸዋለህ።

ምዕራፉን ተመልከት



ዘዳግም 17:5
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በል​ዑል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በዋ​ሸሁ ነበ​ርና ይህ ደግሞ ትልቅ በደል ይሁ​ን​ብኝ።


“ከእ​ን​ስሳ የሚ​ደ​ርስ ሁሉ ሞትን ይሙት።


“ደግሞ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች እን​ዲህ በላ​ቸው፦ ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ወይም በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ ከሚ​ቀ​መጡ እን​ግ​ዶች ማና​ቸ​ውም ሰው ዘሩን ለሞ​ሎክ አገ​ል​ግ​ሎት ቢሰጥ ፈጽሞ ይገ​ደል፤ የሀ​ገሩ ሕዝብ በድ​ን​ጋይ ይው​ገ​ሩት።


“ተሳ​ዳ​ቢ​ውን ከሰ​ፈር ወደ ውጭ አው​ጣው፤ የሰ​ሙ​ትም ሁሉ እጃ​ቸ​ውን በራሱ ላይ ይጫ​ኑ​በት፤ ማኅ​በ​ሩም ሁሉ በድ​ን​ጋይ ይው​ገ​ሩት።”


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ስም ጠርቶ የሚ​ሰ​ድብ ሁሉ ፈጽሞ ይገ​ደል፤ ማኅ​በ​ሩም ሁሉ በድ​ን​ጋይ ይው​ገ​ሩት፤ መጻ​ተኛ ወይም የሀ​ገር ልጅ ቢሆን፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስም ጠርቶ ቢሳ​ደብ ይገ​ደል።


ከግ​ብፅ ምድር ካወ​ጣ​ችሁ፥ ከባ​ር​ነ​ትም ቤት ካዳ​ና​ችሁ ከአ​ም​ላ​ካ​ችሁ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሊያ​ስ​ታ​ችሁ፥ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ትሄ​ድ​ባት ዘንድ ካዘ​ዘህ መን​ገድ ሊያ​ወ​ጣህ ተና​ግ​ሮ​አ​ልና ያ ነቢይ ወይም ሕልም አላሚ ይገ​ደል፤ እን​ዲ​ሁም ክፉ​ውን ነገር ከአ​ንተ አርቅ።


ቢያ​ወ​ሩ​ል​ህም ብት​ሰ​ማም፥ ያን ፈጽ​መህ መር​ምር፤ እነ​ሆም፥ እው​ነት ቢሆን፥ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም መካ​ከል እን​ዲህ ያለ ርኵ​ሰት እንደ ተሠራ ርግጥ ሆኖ ቢገኝ፥


የከ​ተ​ማ​ዉም ሰዎች ሁሉ በድ​ን​ጋይ ደብ​ድ​በው ይግ​ደ​ሉት፤ እን​ዲ​ህም ክፉ​ውን ነገር ከመ​ካ​ከ​ልህ ታር​ቃ​ለህ፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ሰም​ተው ይፈ​ራሉ።


ብላ​ቴ​ና​ዪ​ቱን ወደ አባቷ ቤት ደጅ ያው​ጡ​አት፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ዘንድ ስን​ፍ​ናን አድ​ር​ጋ​ለ​ችና፥ የአ​ባ​ቷ​ንም ቤት አስ​ነ​ው​ራ​ለ​ችና የከ​ተ​ማው ሰዎች በድ​ን​ጋይ ወግ​ረው ይግ​ደ​ሉ​አት፤ እን​ዲ​ሁም ክፉ​ውን ነገር ከመ​ካ​ከ​ልህ ታስ​ወ​ግ​ዳ​ለህ።


ብላ​ቴ​ና​ዪቱ በከ​ተማ ውስጥ ሳለች አል​ጮ​ኸ​ች​ምና፥ ሰው​የ​ውም የባ​ል​ጀ​ራ​ውን ሚስት አስ​ነ​ው​ሮ​አ​ልና በድ​ን​ጋይ ወግ​ረው ይግ​ደ​ሉ​አ​ቸው፤ እን​ዲሁ ክፉ​ውን ነገር ከው​ስ​ጥህ ታስ​ወ​ግ​ዳ​ለህ።


ኢያ​ሱም፥ “ለምን አጠ​ፋ​ኸን? ዛሬ እን​ዳ​ጠ​ፋ​ኸን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዛሬ ያጥ​ፋህ” አለው፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ በድ​ን​ጋይ ወገ​ሩት፤ በእ​ሳ​ትም አቃ​ጠ​ሉት፤ በድ​ን​ጋ​ይም ወገ​ሩ​አ​ቸው።


ኢዮ​አ​ስም በእ​ርሱ ላይ የተ​ነ​ሡ​በ​ትን ሁሉ፥ “ለበ​ዓል እና​ንተ ዛሬ ትበ​ቀ​ሉ​ለ​ታ​ላ​ች​ሁን? ወይስ የበ​ደ​ለ​ውን ትገ​ድ​ሉ​ለት ዘንድ የም​ታ​ድ​ኑት እና​ንተ ናች​ሁን? እርሱ አም​ላክ ከሆ​ነስ የበ​ደ​ለው እስከ ነገ ድረስ ይሙት። መሠ​ዊ​ያ​ዉ​ንም ያፈ​ረ​ሰ​ውን እርሱ ይበ​ቀ​ለው” አላ​ቸው።