ዘዳግም 15:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰባተኛው ዓመት የምሕረት ዓመት ቅርብ ነው፤ አልሰጠውምም ብለህ ክፉ ዐሳብ በልብህ እንዳታስብ ለራስህ ዕወቅ። ወንድምህም ዐይኑን በአንተ ላይ ያከፋል፤ እርሱም ወደ እግዚአብሔር በአንተ ላይ ይጮሃል፤ ኀጢአትም ይሆንብሃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ዕዳ የሚሠረዝበት ሰባተኛው ዓመት ተቃርቧል” የሚል ምናምንቴ ሐሳብ ዐድሮብህ፣ በድኻ ወንድምህ ላይ እንዳትጨክንና ምንም ሳትሰጠው እንዳትቀር፣ እርሱም በአንተ ላይ ወደ እግዚአብሔር ጮኾ በደለኛ እንዳትሆን ተጠንቀቅ! መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ‘ዕዳ የሚሠረዝበት ሰባተኛው ዓመት ተቃርቧል’ የሚል ክፉ ሐሳብ አድሮብህ፥ በችግረኛ ወንድምህ ላይ እንዳትጨክንና ምንም ሳትሰጠው እንዳትቀር፥ እርሱም በአንተ ላይ ወደ ጌታ ጮኾ በደለኛ እንዳትሆን ተጠንቀቅ! አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የዕዳ መሰረዣ ሰባተኛ ዓመት ደርሶአል በማለት ችግረኛ ወገንህን ብድር አትከልክለው፤ እንዲህ ያለ ክፉ ሐሳብም ወደ ልብህ አይግባ፤ ብድር መስጠትን ብትከለክል ችግረኛው ወገንህ ወደ እግዚአብሔር ይጮኻል፤ ስለዚህ በአንተ ላይ እንደ በደል ይቈጠርብሃል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰባተኛው ዓመት የዕዳ ምሕረት ዓመት ቀርቦአል ብለህ ክፉ አሳብ በልብህ እንዳታስብ፥ ለድሀውም ወንድምህ አንዳች የማትሰጥ እንዳትሆን፥ ዓይንህም በእርሱ ላይ ክፉ እንዳይሆን፥ እርሱም ወደ እግዚአብሔር በአንተ ላይ እንዳይጮኽ፥ ኃጢአትም እንዳይሆንብህ ተጠንቀቅ። |
እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፥ “በግብፅ ያለውን የሕዝቤን መከራ በእውነት አየሁ፦ ከአሠሪዎቻቸውም የተነሣ ጩኸታቸውን ሰማሁ፤ ሥቃያቸውንም ዐውቄአለሁ፤
እኔ እግዚአብሔር ለሰው ሁሉ እንደ መንገዱና፥ እንደ ሥራው ፍሬ እሰጥ ዘንድ ልብን እመረምራለሁ፤ ኵላሊትንም እፈትናለሁ።”
ስድስት ዓመት በተፈጸመ ጊዜ፥ የተሸጠላችሁን፥ ስድስትም ዓመት የተገዛላችሁን ዕብራዊ ወንድማችሁን እያንዳንዳችሁ አርነት ታወጡታላችሁ፤ አባቶቻችሁ ግን አልሰሙኝም፤ ጆሮአቸውንም አላዘነበሉም።
ድሃ ነውና፥ ተስፋውም እርሱ ነውና ወደ እግዚአብሔር እንዳይጮኽብህ፥ ኀጢአትም እንዳይሆንብህ ደመወዙን ፀሐይ ሳይገባ በቀኑ ስጠው።