አንተ ግን ፍቺን ትሰጥ ዘንድ፥ የታተመውንም ትፈታ ዘንድ እንድትችል ሰምቻለሁ፤ አሁንም ጽሕፈቱን ታነብብ ዘንድ፥ ፍቺውንም ትነግረኝ ዘንድ ብትችል፥ ሐምራዊ ግምጃ ትለብሳለህ፤ የወርቅም ማርዳ በአንገትህ ዙሪያ አስርልሃለሁ፤ አንተም በመንግሥቴ ላይ ሦስተኛ ገዥ ትሆናለህ።”