አሁንም እኔ ናቡከደነፆር የሰማይን ንጉሥ አመሰግነዋለሁ፤ ከፍ ከፍም አደርገዋለሁ፥ አከብረውማለሁ። ሥራው ሁሉ እውነት፥ መንገዱም ቀና ነውና፤ በትዕቢትም የሚሄዱትን ያዋርድ ዘንድ ይችላልና።