ነገር ግን ሥሩንና ጉቶውን በምድር ውስጥ ተዉት፤ በመስክም ውስጥ በብረትና በናስ ማሰሪያ ታስሮ ይቈይ፤ በሰማይም ጠል ይረስርስ፤ እድል ፋንታውም በምድር ሣር ውስጥ ከአራዊት ጋር ይሁን።