ንጉሡም በፊታቸው ለእግዚአብሔር ሰገደ፥ ናቡከደነፆርም መልሶ እንዲህ አለ፦ መልአኩን የላከ፥ ከአምላካቸውም በቀር ማንንም አምላክ እንዳያመልኩ፥ ለእርሱም እንዳይሰግዱ ሰውነታቸውን አሳልፈው የሰጡትን፥ የንጉሡንም ቃል የተላለፉትን፥ በእርሱ የታመኑትን ባሪያዎቹን ያዳነ፥ የሲድራቅና የሚሳቅ፥ የአብደናጎም አምላክ ይመስገን።