ስለዚህ በዚያን ጊዜ አሕዛብ ሁሉ የመለከቱንና የእንቢልታውን፥ የመሰንቆውንና የክራሩን፥ የበገናውንና የዘፈኑንም ሁሉ ድምፅ በሰሙ ጊዜ፥ ወገኖችና አሕዛብ፥ በልዩ ልዩ ቋንቋም የሚናገሩ ሁሉ ወድቀው፤ ንጉሡ ናቡከደነፆር ላቆመው ለወርቅ ምስል ሰገዱ።