ንጉሡ ናቡከደነፆር በነገሠ በዐሥራ ስምንተኛው ዓመት ቁመቱ ስድሳ ክንድ፥ ወርዱም ስድስት ክንድ የሆነ የወርቅ ምስል አሠራ፤ በባቢሎንም አውራጃ በዱራ ሜዳ አቆመው።