ንጉሡም መለሰ፤ ከለዳውያኑንም፥ “ነገሩ ከእኔ ዘንድ ርቆአል፤ ሕልሙንና ፍቺውን ባታስታውቁኝ፥ ትገደላላችሁ፤ ቤቶቻችሁም የጉድፍ መጣያ ይደረጋሉ።