የዚያን ጊዜም ብረቱና ሸክላው፥ ናሱና ብሩ፥ ወርቁም በአንድነት ተፈጨ፤ በመከርም ጊዜ በአውድማ ላይ እንደአለ እብቅ ሆነ፤ ነፋስም ወሰደው፤ ቦታውም አልታወቀም፤ ምስሉንም የመታው ድንጋይ ታላቅ ተራራ ሆነ፤ ምድርንም ሁሉ ሞላ።