የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




አሞጽ 9:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በቀ​ር​ሜ​ሎስ ራስ ውስጥ ቢሸ​ሸጉ ፈልጌ ከዚያ አወ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በባ​ሕ​ሩም ጥልቅ ውስጥ ከዐ​ይኔ ቢደ​በቁ በዚያ እባ​ቡን አዝ​ዛ​ለሁ፤ እር​ሱም ይነ​ድ​ፋ​ቸ​ዋል፤

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በቀርሜሎስ ጫፍ ላይ ቢሸሸጉም፣ ዐድኜ፣ ፈልጌ ከዚያ አወርዳቸዋለሁ፤ እይዛቸዋለሁም። በጥልቅ ባሕር ውስጥ ከእኔ ቢሸሸጉም፣ በዚያ እባቡ እንዲነድፋቸው አዝዘዋለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በቀርሜሎስም ራስ ላይ ቢሸሸጉ እንኳ አድኜ ከዚያ አወጣቸዋለሁ፤ በጥልቅ ባሕርም ውስጥ ከዓይኔ ቢደበቁ እንኳ ከዚያ እባቡን አዝዛለሁ፥ እርሱም ይነድፋቸዋል፤

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በቀርሜሎስ ተራራ ላይ ወጥተው ቢሸሸጉም ተከታትዬ ከዚያ አወጣቸዋለሁ፤ ወደ ጥልቅ ባሕር ገብተው ከእኔ ለመሰወር ቢሞክሩም እንዲነድፋቸው የባሕሩን ዘንዶ አዛለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በቀርሜሎስም ራስ ውስጥ ቢሸሸጉ ፈልጌ ከዚያ አወጣቸዋለሁ፥ በጥልቅ ባሕርም ውስጥ ከዓይኔ ቢደበቁ ከዚያ እባቡን አዝዛለሁ፥ እርሱም ይነድፋቸዋል፥

ምዕራፉን ተመልከት



አሞጽ 9:3
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እነ​ር​ሱም ቀኑ በመሸ ጊዜ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የአ​ም​ላ​ክን ድምፅ በገ​ነት ውስጥ ሲመ​ላ​ለስ ሰሙ፤ አዳ​ምና ሚስ​ቱም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ም​ላክ ፊት በገ​ነት ዛፎች መካ​ከል ተሸ​ሸጉ።


የባ​ዕድ ልጆች አረጁ፤ ከማ​ን​ከ​ሳ​ቸ​ውም የተ​ነሣ ተሰ​ና​ከሉ።


አን​ተም እን​ዲህ ብለ​ሃል፦ ኀያል እርሱ ምን ያው​ቃል? በድ​ቅ​ድቅ ጨለማ ውስጥ ሆኖ ሊፈ​ርድ ይች​ላ​ልን?


ኀጢ​አ​ትን የሚ​ሠሩ የሚ​ሰ​ወ​ሩ​በት ቦታ የለም።


ዐይ​ኖ​ቻ​ቸው እን​ዳ​ያዩ ይጨ​ልሙ፥ ጀር​ባ​ቸ​ውም ዘወ​ትር ይጉ​በጥ።


በዚ​ያም ቀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በፈ​ጣኑ እባብ ደራ​ጎን ላይ፥ በክ​ፉ​ውም እባብ ደራ​ጎን ላይ ልዩ፥ ታላ​ቅና ብርቱ ሰይ​ፍን ያመ​ጣል። በባ​ሕ​ርም ውስጥ ያለ​ውን ዘንዶ ይገ​ድ​ለ​ዋል።


“እነሆ፥ ብዙ ዓሣ አጥ​ማ​ጆ​ችን እል​ካ​ለሁ፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ እነ​ር​ሱም ያጠ​ም​ዱ​አ​ቸ​ዋል፤ ከዚ​ያም በኋላ ብዙ አድ​ዳ​ኞ​ችን እል​ካ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ከየ​ተ​ራ​ራ​ውና ከየ​ኮ​ረ​ብ​ታው ሁሉ ከየ​ድ​ን​ጋ​ዩም ስን​ጣቂ ውስጥ ያድ​ድ​ኑ​አ​ቸ​ዋል።


እን​ዲ​ህም አለ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከጽ​ዮን ሆኖ ድም​ፁን ከፍ አድ​ርጎ ይና​ገ​ራል፤ ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ሆኖ ቃሉን ይሰ​ጣል፤ የእ​ረ​ኞ​ችም ማሰ​ማ​ሪ​ያ​ዎች ያለ​ቅ​ሳሉ፤ የቀ​ር​ሜ​ሎ​ስም ራስ ይደ​ር​ቃል።”