ወጥቶም ከፍልስጥኤማውያን ጋር ተዋጋ፤ የጌትን ቅጥር፥ የኢያቢስንም ቅጥር፥ የአዛጦንንም ቅጥር አፈረሰ፤ በአዛጦንና በፍልስጥኤማውያንም ሀገር ከተሞችን ሠራ።
አሞጽ 1:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአዛጦን ነዋሪዎችን አጠፋለሁ፤ የአስቀሎናም ሕዝብ ይጠፋለሁ፤ እጄንም በአቃሮን ላይ እመልሳለሁ፤ ከፍልስጥኤማውያን የቀሩትም ይጠፋሉ” ይላል ጌታ እግዚአብሔር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በአስቀሎና በትር የያዘውን፣ የአሽዶድንም ንጉሥ እደመስሳለሁ፤ በፍልስጥኤም ካሉት የመጨረሻው ሰው እስኪሞት ድረስ፣ እጄን በአቃሮን ላይ እዘረጋለሁ፤” ይላል ጌታ እግዚአብሔር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነዋሪዎችዋን ከአዛጦን፥ በትረ መንግሥት የያዘውንም ከአስቀሎና አጠፋለሁ፤ እጄንም በአቃሮን ላይ እመልሳለሁ፥ ከፍልስጥኤማውያንም የቀሩት ይጠፋሉ፥” ይላል ጌታ እግዚአብሔር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በአሽዶድ የሚኖሩትን ሕዝቦችና የአስቀሎናን መሪ አጠፋለሁ፤ የዔቅሮን ከተማ ኗሪዎችንም እቀጣለሁ፤ የተረፉትም ፍልስጥኤማውያን ይሞታሉ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ተቀማጮችን ከአዛጦን አጠፋለሁ፥ በትር የያዘውንም ከአስቀሎና አጠፋለሁ፥ እጄንም በአቃሮን ላይ እመልሳለሁ፥ ከፍልስጥኤማውያንም የቀሩት ይጠፋሉ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር። |
ወጥቶም ከፍልስጥኤማውያን ጋር ተዋጋ፤ የጌትን ቅጥር፥ የኢያቢስንም ቅጥር፥ የአዛጦንንም ቅጥር አፈረሰ፤ በአዛጦንና በፍልስጥኤማውያንም ሀገር ከተሞችን ሠራ።
እጄንም በአንቺ ላይ አመጣለሁ፤ አግልሻለሁ፤ ዝገትሽንም አነጻለሁ፤ ቆርቆሮሽንም ሁሉ አስወግዳለሁ፤ ዐመፀኞችን አጠፋለሁ፤ ሕገ ወጦችንም ከአንቺ አስወግዳለሁ፤ ትዕቢተኞችንም አዋርዳለሁ።
ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ እጄን በፍልስጥኤማውያን ላይ እዘረጋለሁ፤ መኳንንቱንም እቈርጣለሁ፤ የባሕሩንም ዳር ቅሬታ አጠፋለሁ።
“ጢሮስና ሲዶና የፍልስጥኤም አውራጃ ገሊላም ሁሉ ሆይ! ከእናንተ ጋራ ምን አለኝ? እናንተ በቀልን ትበቀሉኛላችሁን? ቂምንስ ትቀየሙኛላችሁን? ፈጥኜ በችኰላ ፍዳን በራሳችሁ ላይ እመልሳለሁ።
በፋርስ ሀገሮችና በግብፅ ሀገሮች ዐውጁና፥ “በሰማርያ ተራሮች ላይ ተሰብሰቡ፤ በውስጥዋም የሆነውን ታላቁን ተአምር፥ በመካካልዋም ያለውን ግፍ ተመልከቱ” በሉ።
እግዚአብሔርም ተናግሮአልና የያዕቆብ ቤት እሳት፥ የዮሴፍም ቤት ነበልባል፥ የዔሳውም ቤት ገለባ ይሆናሉ፤ እነርሱንም ያቃጥሉአቸዋል፤ ይበሉአቸውማል፤ ከዔሳውም ቤት ቅሬታ አይኖርም።
ሰይፍ ሆይ፥ ባልንጀራዬ በሆነው ሰው በእረኛዬ ላይ ንቃ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ እረኛውን ምታ፥ በጎቹም ይበተናሉ፣ እጄንም በታናናሾች ላይ እመልሳለሁ።
አስቀሎና አይታ ትፈራለች፣ ጋዛ ደግሞ አይታ እጅግ ትታመማለች፣ አቃሮንም እንዲሁ፥ ተስፋዋ ይቈረጣልና፣ ንጉሡም ከጋዛ ይጠፋል፥ በአስቀሎናም የሚቀመጥ አይገኝም።
ፍልስጥኤማውያንም ስለ በደል መባእ ለእግዚአብሔር ያቀረቡአቸው የሰውነታቸው ምሳሌ የወርቅ እባጮች እነዚህ ናቸው፦ አንዲቱ ለአዛጦን፥ አንዲቱም ለጋዛ፥ አንዲቱም ለአስቀሎና፥ አንዲቱም ለጌት፥ አንዲቱም ለአቃሮን።