የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ሐዋርያት ሥራ 7:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ደግ​ሞም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አለ፤ ባሮች አድ​ር​ገው በሚ​ገ​ዙ​አ​ቸው ወገ​ኖች እኔ እፈ​ር​ድ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ከዚ​ህም በኋላ ይወ​ጣሉ፤ በዚ​ህም ሀገር ያመ​ል​ኩ​ኛል።’

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ነገር ግን በባርነት የሚገዛቸውን ሕዝብ እኔ ደግሞ እቀጣዋለሁ፤’ ደግሞም ‘ከዚያም አገር ወጥተው በዚህ ስፍራ ያመልኩኛል።’ ይላል እግዚአብሔር።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ደግሞም እግዚአብሔር ‘እንደ ባርያዎች በሚገዙአቸው ሕዝብ ላይ እኔ እፈርድባቸዋለሁ፤ ከዚህም በኋላ ይወጣሉ፤ በዚህም ስፍራ ያመልኩኛል፤’ አለ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ቀጥሎም ‘ባሪያ አድርጎ በሚገዛው ሕዝብ ላይ እፈርድበታለሁ፤ ከዚያም በኋላ ነጻ ወጥተው በዚህ ስፍራ ያመልኩኛል’ ብሎ እግዚአብሔር ተናግሮአል።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ደግሞም እግዚአብሔር፦ ‘እንደ ባሪያዎች በሚገዙአቸው ሕዝብ ላይ እኔ እፈርድባቸዋለሁ፥ ከዚህም በኋላ ይወጣሉ በዚህም ስፍራ ያመልኩኛል’ አለ።

ምዕራፉን ተመልከት



ሐዋርያት ሥራ 7:7
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አሁ​ንም ና፤ ወደ ግብፅ ንጉሥ ወደ ፈር​ዖን እል​ክ​ሃ​ለሁ። ሕዝ​ቤን የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ከግ​ብፅ ምድር ታወ​ጣ​ቸ​ዋ​ለህ።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን ተና​ገ​ረው፤ እን​ዲህ ሲል፥ “በእ​ው​ነት እኔ ከአ​ንተ ጋር እሆ​ና​ለሁ፤ እኔም እንደ ላክ​ሁህ ይህ ለአ​ንተ ምል​ክት ይሆ​ን​ሃል፤ ሕዝ​ቡን ከግ​ብፅ በአ​ወ​ጣህ ጊዜ በዚህ ተራራ ላይ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታመ​ል​ካ​ላ​ችሁ” አለው።