የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ሐዋርያት ሥራ 26:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የአ​ይ​ሁ​ድን ጠባ​ያ​ቸ​ው​ንና ክር​ክ​ራ​ቸ​ውን አጥ​ብ​ቀህ ታው​ቃ​ለ​ህና ታግ​ሠህ ታደ​ም​ጠኝ ዘንድ እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ይኸውም አንተ በተለይ የአይሁድን ልማድና ክርክር ሁሉ በሚገባ ስለምታውቅ ነው፤ ስለዚህ በትዕግሥት እንድታደምጠኝ እለምንሃለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በተለየም አንተ የአይሁድን ሥርዓትና ክርክር ሁሉ ጠንቅቀህ ታውቃለህ፤ ስለዚህ በትዕግሥት እንድታዳምጠኝ እለምንሃለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት



ሐዋርያት ሥራ 26:3
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የታ​ተ​መ​ው​ንም የውል ወረ​ቀት ወሰ​ድሁ፤


ነገር ግን የማ​ይ​ሆ​ነ​ውን እን​ደ​ም​ታ​ስ​ተ​ምር፥ የሙ​ሴ​ንም ሕግ እን​ደ​ም​ታ​ስ​ተ​ዋ​ቸው፥ በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል ያሉ ያመኑ አይ​ሁ​ድ​ንም ልጆ​ቻ​ቸ​ውን እን​ዳ​ይ​ገ​ርዙ፥ የኦ​ሪ​ት​ንም ሕግ እን​ዳ​ይ​ፈ​ጽሙ እን​ደ​ም​ት​ከ​ለ​ክ​ላ​ቸው ስለ አንተ ነግ​ረ​ዋ​ቸ​ዋል።


ሀገረ ገዢ​ውም እን​ዲ​ና​ገር ጳው​ሎ​ስን ጠቀ​ሰው፤ ጳው​ሎ​ስም እን​ዲህ አለ፥ “ከብዙ ዘመን ጀምሮ የዚህ ሕዝብ አስ​ተ​ዳ​ዳሪ እንደ ሆንህ አው​ቃ​ለሁ፤ ጠባ​ያ​ቸ​ው​ንም ታው​ቃ​ለህ። አሁ​ንም ደስ እያ​ለኝ ክር​ክ​ሬን አቀ​ር​ባ​ለሁ።


ነገር ግን ነገር እን​ዳ​ላ​በ​ዛ​ብህ በአ​ጭሩ ትሰ​ማኝ ዘንድ እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ።


ነገር ግን ስለ እርሱ ወደ ጌታዬ የም​ጽ​ፈው የታ​ወቀ ነገር የለ​ኝም። ስለ​ዚህ ከተ​መ​ረ​መረ በኋላ የም​ጽ​ፈ​ውን አገኝ ዘንድ ወደ እና​ንተ ይል​ቁ​ንም ንጉሥ አግ​ሪጳ ሆይ ወደ አንተ አመ​ጣ​ሁት።


“ንጉሥ አግ​ሪጳ ሆይ፥ አይ​ሁድ እኔን ስለ ከሰ​ሱ​በት ነገር ሁሉ ዛሬ በአ​ንተ ዳኝ​ነት እከ​ራ​ከር ዘንድ ስለ ተገ​ባኝ ራሴን እንደ ተመ​ሰ​ገነ አድ​ርጌ እቈ​ጥ​ረ​ዋ​ለሁ።


በፊቱ ገልጬ የም​ና​ገ​ር​ለት እርሱ ራሱ ንጉሥ አግ​ሪጳ ያው​ቅ​ል​ኛል፤ ከዚ​ህም የሚ​ሳ​ተው ነገር ያለ አይ​መ​ስ​ለ​ኝም፤ ወደ ጎን የተ​ሰ​ወረ አይ​ደ​ለ​ምና።


ንጉሥ አግ​ሪጳ ሆይ፥ ዐሥራ ሁለቱ ነገ​ዶ​ቻ​ችን በመ​ዓ​ል​ትም በሌ​ሊ​ትም እር​ሱን እያ​ገ​ለ​ገሉ ወደ እር​ስዋ ይደ​ርሱ ዘንድ ተስፋ ያደ​ር​ጋሉ፤ አይ​ሁ​ድም የሚ​ከ​ስ​ሱኝ ስለ​ዚህ ተስፋ ነው።


ከሦ​ስት ቀንም በኋላ ጳው​ሎስ የአ​ይ​ሁ​ድን ታላ​ላቅ ሰዎች ሰበ​ሰ​ባ​ቸው፤ በተ​ሰ​በ​ሰ​ቡም ጊዜ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ እኔ በሕ​ዝ​ቡም ላይ ቢሆን፥ በአ​ባ​ቶ​ቻ​ች​ንም ሕግ ላይ ቢሆን ያደ​ረ​ግ​ሁት ክፉ ነገር የለም፤ ነገር ግን በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም እንደ ታሰ​ርሁ ለሮም ሰዎች አሳ​ል​ፈው ሰጡኝ።


የና​ዝ​ሬቱ ኢየ​ሱስ ይህን ቤተ መቅ​ደስ ያፈ​ር​ሰ​ዋል፤ ሙሴም የሰ​ጠ​ንን ኦሪ​ታ​ች​ንን ይሽ​ራል ሲል ሰም​ተ​ነ​ዋል።”


ትን​ቢት ብና​ገር፥ የተ​ሰ​ው​ረ​ውን ሁሉ፥ ጥበ​ብ​ንም ሁሉ ባውቅ፥ ተራራ እስከ ማፍ​ለስ የሚ​ያ​ደ​ርስ ፍጹም እም​ነ​ትም ቢኖ​ረኝ ፍቅር ከሌ​ለኝ ከንቱ ነኝ።


“በግ​ዛ​ቱም በተ​ቀ​መጠ ጊዜ ከሌ​ዋ​ው​ያን ካህ​ናት ወስዶ ይህን ሁለ​ተኛ ሕግ ለራሱ በመ​ጽ​ሐፍ ይጻፍ።