የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ሐዋርያት ሥራ 11:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

“ወደ አል​ተ​ገ​ረ​ዙት ሰዎች ቤት ገብ​ተህ አብ​ረ​ሃ​ቸው በል​ተ​ሃል” አሉት።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እንዲህም አሉት፤ “ወዳልተገረዙ ሰዎች ገብተህ ከእነርሱ ጋራ በላህ።”

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

“ወዳልተገረዙ ሰዎች ገብተህ ከእነርሱ ጋር በላህ፤” አሉት።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

“ስለምን ወዳልተገረዙ ሰዎች ቤት ገብተህ ከእነርሱ ጋር በላህ?” በማለት ወቀሱት።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

“ወዳልተገረዙ ሰዎች ገብተህ ከእነርሱ ጋር በላህ” አሉት።

ምዕራፉን ተመልከት



ሐዋርያት ሥራ 11:3
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ፈሪሳውያንም አይተው ደቀ መዛሙርቱን “መምህራችሁ ከቀራጮችና ከኀጢአተኞች ጋር አብሮ ስለ ምን ይበላል?” አሉአቸው።


ጻፎ​ችና ፈሪ​ሳ​ው​ያ​ንም፥ “ይህስ ኀጢ​ኣ​ተ​ኞ​ችን ይቀ​በ​ላል፤ አብ​ሮ​አ​ቸ​ውም ይበ​ላል” ብለው አን​ጐ​ራ​ጐሩ።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስ​ንም ከቀ​ያፋ ወደ ፍርድ አደ​ባ​ባይ ወሰ​ዱት፤ አይ​ሁድ ግን ፈጽሞ ስለ ነጋ የፋ​ሲ​ካ​ውን በግ ሳይ​በሉ እን​ዳ​ይ​ረ​ክሱ ወደ ፍርድ አደ​ባ​ባይ አል​ገ​ቡም።


እር​ሱም ተቀ​ብሎ አሳ​ደ​ራ​ቸው፤ በማ​ግ​ሥ​ቱም ተነ​ሥቶ አብ​ሮ​አ​ቸው ሄደ፤ በኢ​ዮጴ ከተማ ከሚ​ኖ​ሩት ወን​ድ​ሞ​ችም አብ​ረ​ውት የሄዱ ነበሩ።


ጴጥ​ሮ​ስም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ለአ​ይ​ሁ​ዳዊ ሰው ሄዶ ከባ​ዕድ ወገን ጋር መቀ​ላ​ቀል እን​ደ​ማ​ይ​ገ​ባው ታው​ቃ​ላ​ችሁ፤ ለእኔ ግን ከሰው ማን​ንም ቢሆን እን​ዳ​ል​ጸ​የ​ፍና ርኩስ ነው እን​ዳ​ልል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አሳ​የኝ።


አሁ​ንም ወደ ኢዮጴ ከተማ ላክና በባ​ሕር አቅ​ራ​ቢያ ባለ​ችው በቍ​ር​በት ፋቂው በስ​ም​ዖን ቤት የሚ​ኖ​ረ​ውን ጴጥ​ሮስ የተ​ባ​ለ​ውን ስም​ዖ​ንን ይጥ​ሩ​ልህ፤ እርሱ መጥቶ የም​ት​ድ​ን​በ​ትን ይነ​ግ​ር​ሃል።


በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስም ስም እን​ዲ​ጠ​መቁ አዘ​ዛ​ቸው። ከዚ​ህም በኋላ ጥቂት ቀን አብ​ሮ​አ​ቸው እን​ዲ​ቀ​መጥ ጴጥ​ሮ​ስን ማለ​ዱት።


አሁ​ንም ከወ​ን​ድ​ሞች መካ​ከል ዘማዊ፥ ወይም ገን​ዘ​ብን የሚ​መኝ፥ ወይም ጣዖ​ትን የሚ​ያ​መ​ልክ፥ ወይም ዐመ​ፀኛ፥ ወይም ተራ​ጋሚ፥ ወይም ሰካ​ራም፥ ወይም የሚ​ቀማ ቢኖር እን​ደ​ዚህ ካለ ሰው ጋር አንድ እን​ዳ​ት​ሆኑ ጻፍ​ሁ​ላ​ችሁ፥ እን​ደ​ዚህ ካለው ሰው ጋር መብ​ልም እንኳ አት​ብሉ፤


ሰዎች ከያ​ዕ​ቆብ ዘንድ ከመ​ም​ጣ​ታ​ቸው በፊት፥ ከአ​ረ​ማ​ው​ያን ጋር ይበላ ነበ​ርና፥ በመጡ ጊዜ ግን ተለ​ያ​ቸው፤ ከአ​ይ​ሁድ ወገን የሆ​ኑ​ትን ፈር​ቶ​አ​ልና።


ማንም ወደ እናንተ ቢመጣ ይህንም ትምህርት ባያመጣ በቤታችሁ አትቀበሉት፤ ሰላምም አትበሉት፤