የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




2 ሳሙኤል 1:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ወሬ​ውን ያመ​ጣ​ለት ጎል​ማ​ሳም አለ፥ “በጌ​ላ​ቡሄ ተራራ ተዋ​ግ​ተው ወደቁ፤ እነ​ሆም፥ ሳኦል በጦሩ ላይ ተኝቶ ነበር፤ ሰረ​ገ​ሎ​ችና ፈረ​ሰ​ኞ​ችም ተከ​ት​ለው ደረ​ሱ​በት።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ወሬ ነጋሪው ወጣትም እንዲህ አለ፤ “ድንገት ወደ ጊልቦዓ ተራራ ወጥቼ ነበር፤ እዚያም ሳኦል ጦሩን ተደግፎ ሳለ፣ የሠረገሎችና የፈረሰኞች አለቆች ተከታተሉት።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ወሬ ነጋሪው ወጣትም እንዲህ አለ፤ “ድንገት ወደ ጊልቦዓ ተራራ ወጥቼ ነበር፤ እዚያም ሳኦል ጦሩን ተመርኩዞ ሳለ፥ ሠረገሎችና ፈረሰኞች ተከትለው ደረሱበት፤

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ወጣቱም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “እኔ በጊልቦዓ ተራራ ላይ ነበርኩ፤ ሳኦል ጦሩን ተደግፎ ሳለ የጠላት ሠረገሎችና ፈረሰኞች ወደ እነርሱ ሲጠጉ አየሁ፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ወሬኛውም ጕልማሳ አለ፦ በድንገት ወደ ጊልቦዓ ተራራ መጣሁ፥ እነሆም፥ ሳኦል ጦሩን ተመርኩዞ ቆሞ ነበር፥ ሰረገሎችና ፈረሰኞችም ተከትለው ደረሱበት።

ምዕራፉን ተመልከት



2 ሳሙኤል 1:6
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እና​ንተ የጌ​ላ​ቡሄ ተራ​ሮች ሆይ፥ ዝና​ብና ጠል አይ​ው​ረ​ድ​ባ​ችሁ፤ ቍር​ባ​ን​ንም የሚ​ያ​በ​ቅል እርሻ አይ​ሁ​ን​ባ​ችሁ። የኀ​ያ​ላን ጋሻ በዚያ ወድ​ቆ​አ​ልና፤ የሳ​ኦ​ልም ጋሻ ዘይት አል​ተ​ቀ​ባ​ምና።


ዳዊ​ትም ወሬ​ውን ያመ​ጣ​ለ​ትን ጐል​ማሳ፥ “ሳኦ​ልና ልጁ ዮና​ታን እንደ ሞቱ እን​ዴት ዐወ​ቅህ?” አለው።


ወደ ኋላ​ውም ዘወር አለና እኔን አይቶ ጠራኝ፤ እኔም፦ እነ​ሆኝ አልሁ።


አንድ ካህ​ንም በዚ​ያች መን​ገድ ሲወ​ርድ ድን​ገት አገ​ኘው፤ አይ​ቶም አል​ፎት ሄደ።


ሄደችም፥ ከአጫጆችም በኋላ በእርሻ ውስጥ ቃረመች፣ እንደ አጋጣሚውም የአቤሜሌክ ወገን ወደ ነበረው ወደ ቦዔዝ እርሻ ደረሰች።


ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ተሰ​ብ​ስ​በው መጡ፤ በሱ​ነ​ምም ሰፈሩ፤ ሳኦ​ልም እስ​ራ​ኤ​ልን ሁሉ ሰበ​ሰበ፤ በጌ​ላ​ቡ​ሄም ሰፈሩ።


ወደ​ም​ት​ሄ​ድ​በ​ትም ተመ​ል​ከቱ፤ በድ​ን​በ​ሩም መን​ገድ ላይ ወደ ቤት​ሳ​ሚስ ብት​ወጣ ይህን እጅግ ክፉ ነገር ያደ​ረ​ገ​ብን እርሱ ነው፤ አለ​ዚ​ያም እን​ዲ​ያው መጥ​ቶ​ብ​ናል እንጂ የመ​ታን የእ​ርሱ እጅ እን​ዳ​ል​ሆነ እና​ው​ቃ​ለን።”