ፈቃዱንም ታደርግ እንደ ሆነ፥ አታደርግም እንደ ሆነ መረመረህ፤ በምድርም መንገድህን ብታሣምር እግዚአብሔር መንገድህን ያከናውንልሃል፤ እጅህንም ያኖርህበትን ሁሉ ያከናውንልሃል፤ ይባርክልሃልም፤ ጥንተ ጠላቶችህንና የዕለት ጠላቶችህንም ያስገዛልሃል።