የታሰሩትን የሚፈታ እርሱ ነው፤ የሞቱትንም የሚያስነሣ እርሱ ነው፤ የይቅርታ ጠል ከእርሱ ዘንድ ነውና ሥጋቸው የፈረሰና የበሰበሰ፥ እንደ ትቢያም የሆነ ሰዎችን በወደደ ጊዜ ያስነሣቸዋል።