ነገር ግን የእግዚአብሔርን ቃልና ሕግ መስማትን እንቢ ብትል፥ በፍርዱም ባትኖር ፍርዱ ሁሉ እውነት ነውና ከአንተ አስቀድሞ እንደ ነበሩ፥ በሚገባም እግዚአብሔርን እንደማያመልኩት፥ በቀና ፍርዱም ጸንተው እንዳላመኑ ወንጀለኞች ከእግዚአብሔር እጅ የምታመልጥበት የለም።