የመቃቢስንም ልጆች ያማሩ እንደ ሆኑና ፈጣሪያቸው እግዚአብሔርን እንደሚያመልኩት ባዩአቸው ጊዜ እንዲሠዉና ከረከሰችውም መሥዋዕት እንዲበሉ የጣዖታቱ ካህናት ያስትዋቸው ዘንድ ወደዱ፤ እነዚህ የተባረኩ የመቃቢስ ልጆች ግን እንቢ አሏቸው።