እነርሱም፥ “እግዚአብሔር ፈጣሪህ እንደ ሆነ አስብ” እያሉ የሚገባውን ሁሉ ነገሩት፤ “ከዚህም ትዕቢትህ የሚሽርህና ከአባትህ ከዲያብሎስ ጋራ ወደ ታች ወደ ገሃነም የሚያወርድህ አለ፤ በዚያም አንተን የበደልንህ በደል ሳይኖር፥ ፈጣሪያችን እግዚአብሔርንም እያመለክን ሳለን፥ እግዚአብሔርነቱንም በመፍራት እየሰገድንለት ሳለን በእሳት እንዳቃጠልኸን ፍዳህን ሁሉ ትጨርሳለህ።