ዳግመኛም ስሙ ብኤል ፌጎር የሚባል ጣዖትን ያመልኩ ነበር፤ እንደ ፈጣሪያቸው እንደ እግዚአብሔርም ያመልኩትና ይታመኑት ነበር። እርሱ ግን ደንቆሮና ዲዳ ስለሆነ የሚያየውና የሚሰማው የለም፤ የሰው እጅ ሥራ ጣዖት ነውና፤ ብርና ወርቅን የሚሠራ አንጥረኛ የሠራው፥ ትንፋሽና ዕውቀት የሌለው የሰው እጅ ሥራ ነው፤