ይህንም ነገር ተናግሮ ሳይጨርስ ስሙ ጥልምያኮስ የሚባል መልአከ ሞት ወርዶ ልቡን መታው፤ በዚያችም ሰዓት ሞተ፤ ፈጣሪውን አላመሰገነውምና ከትዕቢቱ ብዛት፥ ከሥራውም ክፋት የተነሣ ከአማረ ኑሮው ተለይቶ ጠፋ።