እርሱ ግን በምንም አንድ ጊዜ አላጠፋቸውም፤ ስለ አባቶቻቸው ይራራላቸዋልና የሚራራላቸው ስለ ራሳቸው አይደለም። በእውነት የነገሡ፥ በፈጣሪያቸውም ፊት በቀና ሕግ ጸንተው የኖሩ አባቶቻቸውን አብርሃምንና ይስሐቅን ያዕቆብንም ይወዳቸዋልና ነው እንጂ።