የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




2 ቆሮንቶስ 9:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ምና​ል​ባት የመ​ቄ​ዶ​ንያ ሰዎች ከእኔ ጋር ቢመ​ጡና ሳታ​ዘ​ጋጁ ቢያ​ገ​ኙ​አ​ችሁ እና​ንተ ታፍ​ራ​ላ​ችሁ ባል​ልም እኛ ስለ እና​ንተ ከነ​ገ​ር​ና​ቸው የተ​ነሣ እና​ፍ​ራ​ለን።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ምናልባት የመቄዶንያ ሰዎች ከእኔ ጋራ መጥተው ሳትዘጋጁ ቢያገኟችሁ፣ እናንተ ብቻ ሳትሆኑ እኛም ያን ያህል በእናንተ በመመካታችን እናፍራለን።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ምናልባት የመቄዶንያ ሰዎች ከእኔ ጋር ቢመጡና ሳትዘጋጁ ቢያገኟችሁ፥ ያን ያህል ማለታችን እንድታፍሩ ባይሆንም፥ እንዲህ በመመካታችን ግን እንድናፍር ያደርገናል።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የመቄዶንያ ሰዎች ከእኔ ጋር ወደ እናንተ መጥተው ያልተዘጋጃችሁ ሆናችሁ ቢያገኙአችሁ በእናንተ በመመካታችን እናፍራለን፤ እናንተማ በጣም ታፍራላችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ምናልባት የመቄዶንያ ሰዎች ከእኔ ጋር ቢመጡ፥ ያልተዘጋጃችሁም ሆናችሁ ቢያገኙአችሁ፥ እናንተ እንድታፍሩ አላልንም እኛ ግን በዚህ እምነታችን እንድናፍር አይሁን።

ምዕራፉን ተመልከት



2 ቆሮንቶስ 9:4
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

መቄ​ዶ​ን​ያና አካ​ይያ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ቅዱ​ሳን መካ​ከል ላሉ ድሆች አስ​ተ​ዋ​ጽ​ፅኦ ለማ​ድ​ረግ ተባ​ብ​ረ​ዋ​ልና።


እኔ ስመጣ ይህ የገ​ን​ዘብ ማዋ​ጣት ያን​ጊዜ እን​ዳ​ይ​ሆን፥ ከእ​ና​ንተ ሰው ሁሉ በየ​ሳ​ም​ንቱ እሑድ የተ​ቻ​ለ​ውን ያወ​ጣጣ፤ ያገ​ኘ​ው​ንም በቤቱ ይጠ​ብቅ።


ይህም ቢሆን የም​ና​ገ​ረው ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ገባ አይ​ደ​ለም፤ ነገር ግን ስለ​ዚ​ህች ትም​ክ​ሕቴ እንደ ሰነፍ እና​ገ​ራ​ለሁ።


አሁ​ንም መዋ​ደ​ዳ​ች​ሁ​ንና እኛም በእ​ና​ንተ የም​ን​መ​ካ​በ​ትን ሥራ በአ​ብ​ያተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ናት ፊት በግ​ልጥ አሳ​ዩ​አ​ቸው።


እና​ንተ እን​ደ​ም​ት​ተጉ አው​ቃ​ለ​ሁና፤ ስለ​ዚ​ህም “የአ​ካ​ይያ ሰዎች እኮ ከአ​ምና ጀምሮ አዘ​ጋ​ጅ​ተ​ዋል” ብዬ በመ​ቄ​ዶ​ንያ ሰዎች ዘንድ አመ​ሰ​ገ​ን​ኋ​ችሁ፤ እነ​ሆም የእ​ና​ንተ መፎ​ካ​ከር ብዙ​ዎ​ችን ሰዎች አት​ግ​ቶ​አ​ቸ​ዋል።


እኔ ጳውሎስ “እኔ እመልሰዋለሁ፤” ብዬ በእጄ እጽፋለሁ፤ ከዚህም በላይ ለእኔ የራስህ ደግሞ ብድር እንዳለብህ አልልህም።