የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




2 ቆሮንቶስ 3:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን አሁን ደግሞ ራሳ​ች​ንን እያ​መ​ሰ​ገን ልን​ነ​ግ​ራ​ችሁ እን​ጀ​ም​ራ​ለ​ንን? ወይስ እንደ ሌሎች ስለ እኛ ወደ እና​ንተ ደብ​ዳቤ እን​ዲ​ጽ​ፉ​ላ​ችሁ፥ ወይስ እና​ንተ ትጽ​ፉ​ልን ዘንድ የም​ን​ሻው አለን?

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እንደ ገና ራሳችንን ልናመሰግን እንጀምራለንን? ወይስ እንደ ሌሎቹ ለእናንተ ወይም ከእናንተ የተጻፈ የምስጋና ደብዳቤ ያስፈልገን ይሆንን?

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እንደገና ራሳችንን ልናመሰግን እንጀምራለንን? ወይስ አንዳንዶች እንደሚያደርጉት ለእናንተ ወይም ከእናንተ የተጻፈ የምስጋና ደብዳቤ ያስፈልገን ይሆንን?

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እንደገና ራሳችንን ልናመሰግን እንጀምራለንን? ወይስ አንዳንዶች እንደሚያደርጉት ለእናንተ ወይም ከእናንተ የድጋፍ ደብዳቤ ያስፈልገን ይሆን?

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እንደ ገና ራሳችንን ልናመሰግን እንጀምራለንን? ወይስ እንደ ሌሎች የማመስገኛ መልእክት ወደ እናንተ ወይስ ከእናንተ ያስፈልገን ይሆንን?

ምዕራፉን ተመልከት



2 ቆሮንቶስ 3:1
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ወደ አካ​ይ​ያም ሊሄድ በወ​ደደ ጊዜ ወን​ድ​ሞች አጽ​ና​ኑት፤ እን​ዲ​ቀ​በ​ሉ​ትም ወደ ደቀ መዛ​ሙ​ርት ጻፉ​ለት፤ ወደ እነ​ር​ሱም በደ​ረሰ ጊዜ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋ ላመ​ኑት ብዙ አስ​ተ​ማ​ራ​ቸው፤ ትልቅ ርዳ​ታም ረዳ​ቸው።


ለክ​ን​ክ​ራ​ኦስ ቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን የም​ት​ላ​ላ​ከ​ውን እኅ​ታ​ች​ንን ፌቤ​ንን አደራ እላ​ች​ኋ​ለሁ፤


እኔም ሁሉን በሁሉ ነገር ደስ እን​ዳ​ሰኝ ይድኑ ዘንድ የብ​ዙ​ዎ​ችን ተድላ እሻ​ለሁ እንጂ የራ​ሴን ተድላ የምሻ አይ​ደ​ለ​ሁ​ምና።


በመ​ጣሁ ጊዜም ስጦ​ታ​ች​ሁን ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ያደ​ርሱ ዘንድ የመ​ረ​ጣ​ች​ኋ​ቸ​ውን ሰዎች መል​እ​ክ​ቴን ጨምሬ እል​ካ​ቸ​ዋ​ለሁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሰጠኝ ጸጋ መጠን እንደ ብልህ የጠ​ራ​ቢ​ዎች አለቃ ሆኜ እኔ መሠ​ረት ጣልሁ፤ ሌላ​ውም በእ​ርሱ ላይ ያን​ጻል፤ እያ​ን​ዳ​ንዱ ግን በእ​ርሱ ላይ እን​ዴት እን​ደ​ሚ​ያ​ንጽ ይጠ​ን​ቀቅ።


በክ​ር​ስ​ቶስ ብዙ መም​ህ​ራን ቢኖ​ሩ​አ​ች​ሁም አባ​ቶ​ቻ​ችሁ ብዙ​ዎች አይ​ደ​ሉም፤ እኔ በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ በት​ም​ህ​ርት ወል​ጄ​አ​ች​ኋ​ለ​ሁና።


እነ​ርሱ ራሳ​ቸ​ውን በአ​ሰ​ቡ​ትና በገ​መ​ገ​ሙት መጠን ራሳ​ቸ​ውን ከሚ​ያ​መ​ሰ​ግ​ኑት ሰዎች ጋር ራሳ​ች​ንን ልን​ቈ​ጥር፥ ወይም ራሳ​ች​ንን ልና​ስ​ተ​ያይ አን​ደ​ፍ​ርም፤ እነ​ርሱ ራሳ​ቸ​ውም የሚ​ና​ገ​ሩ​ትን ትር​ጕ​ሙን አያ​ው​ቁ​ትም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያከ​በ​ረው ብቻ ይከ​ብ​ራል እንጂ ራሱን የሚ​ያ​ከ​ብር የተ​መ​ረጠ አይ​ደ​ለም።


እና​ን​ተን ለማ​ነጽ እንጂ፥ እና​ን​ተን ለማ​ፍ​ረስ ያይ​ደለ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ና​ንተ ላይ በሰ​ጠን ሥል​ጣን እጅግ የተ​መ​ካ​ሁት መመ​ካት ቢኖር አላ​ፍ​ርም።


እነሆ እና​ንተ ስላ​ገ​በ​ራ​ች​ሁኝ በመ​መ​ካቴ ሰነፍ ሆንሁ፤ ለእ​ኔማ በእ​ና​ንተ ዘንድ ልከ​ብ​ርና እና​ን​ተም ምስ​ክ​ሮች ልት​ሆ​ኑኝ ይገ​ባኝ ነበር፤ እኔ እንደ ኢም​ንት ብሆ​ንም ዋና​ዎቹ ሐዋ​ር​ያት ሁሉ ከሠ​ሩት ሥራ ያጐ​ደ​ል​ሁ​ባ​ችሁ የለ​ምና።


እኛስ ደግሞ ስለ ራሳ​ችን የም​ን​ከ​ራ​ከ​ራ​ችሁ ይመ​ስ​ላ​ች​ኋ​ልን? በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በክ​ር​ስ​ቶስ ሆነን እን​ና​ገ​ራ​ለን፤ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ ይህ ሁሉ ግን እና​ንተ ትታ​ነጹ ዘንድ ነው።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል በሌላ ቀላ​ቅ​ለው እን​ደ​ሚ​ሸ​ቅጡ እንደ ብዙ​ዎች አይ​ደ​ለ​ን​ምና፤ በቅ​ን​ነት ግን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ተላከ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በክ​ር​ስ​ቶስ እን​ና​ገ​ራ​ለን።


በዚህ ደግሞ በእ​ና​ንተ ዘንድ ራሳ​ች​ንን የም​ና​መ​ሰ​ግን አይ​ደ​ለም፤ ነገር ግን እኛ እን​ደ​ም​ን​መ​ካ​ባ​ችሁ፥ እና​ን​ተም በእኛ እን​ድ​ት​መኩ፥ ከልብ ሳይ​ሆን ለሰው ይም​ሰል በሚ​መኩ ሰዎች ዘንድ መልስ እን​ዲ​ሆ​ና​ችሁ ምክ​ን​ያ​ትን እን​ሰ​ጣ​ች​ኋ​ለን።