የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




1 ሳሙኤል 29:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም አለ​ቆች በመቶ በመቶ፥ በሺህ በሺህ እየ​ሆኑ ያልፉ ነበር፤ ዳዊ​ትና ሰዎ​ቹም ከአ​ን​ኩስ ጋር በኋ​ለ​ኛው ጭፍራ በኩል ያልፉ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የፍልስጥኤማውያን ገዦች በመቶና በሺሕ ሆነው ሲዘምቱ፣ ዳዊትና ሰዎቹም ከአንኩስ ጋራ ደጀን ሆነው ይከተሉ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የፍልስጥኤማውያን ገዢዎች በመቶና በሺህ ሆነው ሲዘምቱ፥ ዳዊትና ሰዎቹም ከአኪሽ ጋር ደጀን ሆነው ይከተሉ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አምስቱም የፍልስጥኤም ነገሥታት በመቶና በሺህ ከተመደቡ ሰልፈኞቻቸው ጋር ዘመቱ፤ ዳዊትና ተከታዮቹም የአኪሽ ደጀን ጦር ሆነው ዘመቱ፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የፍልስጥኤማውያንም አለቆች በመቶ በመቶ በሺህ በሺህ እየሆኑ ያልፉ ነበር፥ ዳዊትና ሰዎቹም ከአንኩስ ጋር በኋለኛው ጭፍራ በኩል ያልፉ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት



1 ሳሙኤል 29:2
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዳዊ​ትም ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ጋር ሳኦ​ልን ሊወጋ በመጣ ጊዜ ከም​ናሴ ወገን ሰዎች ወደ ዳዊት ከዱ፤ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን አለ​ቆች ግን፥ “በራ​ሳ​ችን ላይ ጉዳት አድ​ርጎ ወደ ጌታው ወደ ሳኦል ይመ​ለ​ሳል” ሲሉ ተማ​ክ​ረው ሰድ​ደ​ው​ታ​ልና እርሱ አል​ረ​ዳ​ቸ​ውም።


ከሠ​ራ​ዊቱ ሁሉ በኋላ የዳን ልጆች ሰፈር በሥ​ር​ዐ​ታ​ቸው ከየ​ሠ​ራ​ዊ​ታ​ቸው ጋር ተጓዘ፤ በሠ​ራ​ዊ​ቱም ላይ የአ​ሚ​ሳዲ ልጅ አኪ​ያ​ዜር አለቃ ነበረ።


በግ​ብፅ ፊት ካለው ምድረ በዳ ጀምሮ ለአ​ም​ስቱ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤም ግዛ​ቶች ለጋዛ፥ ለአ​ዛ​ጦን፥ ለአ​ስ​ቀ​ሎና፥ ለጌት፥ ለአ​ቃ​ሮን፥ እን​ዲ​ሁም ለኤ​ዌ​ዎ​ና​ው​ያን በተ​ቈ​ጠ​ረ​ችው በከ​ነ​ዓን ግራ በኩል እስ​ካ​ለ​ችው እስከ አቃ​ሮን ዳርቻ ድረስ ነው፤


እነ​ር​ሱም፥ “ስለ መቅ​ሠ​ፍቱ የም​ን​ሰ​ጠው የበ​ደል መባእ ምን​ድን ነው?” አሉ። እነ​ር​ሱም እን​ዲህ አሉ፥ “እና​ን​ተ​ንና አለ​ቆ​ቻ​ች​ሁን፥ ሕዝ​ባ​ች​ሁ​ንም ያገ​ኘች መቅ​ሠ​ፍት አን​ዲት ናትና እንደ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን አለ​ቆች ቍጥር አም​ስት የወ​ርቅ እባ​ጮች፥ አም​ስ​ትም የወ​ርቅ አይ​ጦች አቅ​ርቡ።