የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




1 ሳሙኤል 19:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሳኦ​ልም ለልጁ ለዮ​ና​ታ​ንና ለብ​ላ​ቴ​ኖቹ ሁሉ ዳዊ​ትን ይገ​ድሉ ዘንድ ነገ​ራ​ቸው። የሳ​ኦል ልጅ ዮና​ታን ግን ዳዊ​ትን እጅግ ይወ​ድ​ደው ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሳኦል ዳዊትን እንዲገድሉት ለልጁ ለዮናታንና ለባልሟሎቹ ነገራቸው። ዮናታን ግን ዳዊትን እጅግ ይወድደው ነበር፣

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሳኦል ዳዊትን እንዲገድሉት ለልጁ ለዮናታንና ለባለሟሎቹ ነገራቸው፤ ዮናታን ግን ዳዊትን እጅግ ይወደው ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሳኦል ዳዊትን ሊገድለው ማቀዱን ለልጁ ለዮናታንና ባለሟሎቹ ለሆኑት ባለሥልጣኖች ሁሉ ነገረ፤ ነገር ግን ዮናታን ዳዊትን እጅግ ይወደው ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሳኦልም ለልጁ ለዮናታንና ለባሪያዎቹ ሁሉ ዳዊትን ይገድሉ ዘንድ ነገራቸው። የሳኦል ልጅ ዮናታን ግን ዳዊትን እጅግ ይወድድ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት



1 ሳሙኤል 19:1
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እነ​ር​ሱም ወደ እነ​ርሱ ሳይ​ቀ​ርብ ከሩቅ አስ​ቀ​ድ​መው አዩት፥ ይገ​ድ​ሉ​ትም ዘንድ በእ​ርሱ ላይ ተማ​ከሩ።


የኢ​ያ​ቡ​ስ​ቴ​ንም ራስ ይዘው ወደ ዳዊት ወደ ኬብ​ሮን መጡ፤ ንጉ​ሡ​ንም፥ “ነፍ​ስ​ህን ይሻ የነ​በ​ረው የጠ​ላ​ትህ የሳ​ኦል ልጅ የኢ​ያ​ቡ​ስቴ ራስ እነሆ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ዛሬ ከጠ​ላ​ትህ ከሳ​ኦ​ልና ከዘሩ ለጌ​ታ​ችን ለን​ጉሥ በቀ​ሉን መለ​ሰ​ለት” አሉት።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ዳዊት ለሳ​ኦል መን​ገ​ሩን በፈ​ጸመ ጊዜ የዮ​ና​ታን ነፍስ በዳ​ዊት ነፍስ ታሰ​ረች፤ ዮና​ታ​ንም እንደ ነፍሱ ወደ​ደው።


ሳኦ​ልም አላ​ቸው፥ “የን​ጉ​ሥን ጠላ​ቶች ይበ​ቀል ዘንድ ከመቶ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ሸለ​ፈት በቀር ንጉሥ ማጫ አይ​ሻም ብላ​ችሁ ለዳ​ዊት ንገ​ሩት” አላ​ቸው። ሳኦል ግን ይህን ማለቱ በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን እጅ ይጥ​ለው ዘንድ አስቦ ነው።


ዮና​ታ​ንም እንደ ነፍሱ ስለ ወደ​ደው ዮና​ታ​ንና ዳዊት ቃል ኪዳን አደ​ረጉ።


ሳኦ​ልም እጅግ ተቈጣ፤ ይህም ነገር ሳኦ​ልን አስ​ከ​ፋው፤ እር​ሱም፥ “ለዳ​ዊት ዐሥር ሺህ ሰጡት፤ ለእኔ ግን ሺህ ብቻ ሰጡኝ፤ ከመ​ን​ግ​ሥት በቀር ምን ቀረ​በት?” አለ።


ከዚ​ያም ቀን ጀምሮ ሳኦል ዳዊ​ትን ሁል​ጊዜ ይጠ​ባ​በ​ቀው ነበር።


ዮና​ታ​ንም፥ “አባቴ ሳኦል ሊገ​ድ​ልህ ፈል​ጎ​አል፤ አሁን እን​ግ​ዲህ ለነ​ገው ተጠ​ን​ቅ​ቀህ ተሸ​ሸግ፤ በስ​ው​ርም ተቀ​መጥ።


ዳዊ​ትም ከአ​ው​ቴ​ዘ​ራማ ሸሸ፤ ወደ ዮና​ታ​ንም መጣ፤ እን​ዲ​ህም አለው፥ “ምን አደ​ረ​ግሁ? ምንስ በደ​ልሁ? ነፍ​ሴ​ንም ይሻት ዘንድ በአ​ባ​ትህ ፊት ጥፋ​ቴና ኀጢ​አቴ ምን​ድን ነው?”


ሦስት ቀንም ያህል ቈይ፤ ከዚ​ህም በኋላ በፈ​ለ​ገህ ጊዜ ትመ​ጣና ነገሩ በተ​ደ​ረ​ገ​በት ቀን በተ​ሸ​ሸ​ግ​ህ​በት ስፍራ ትቀ​መ​ጣ​ለህ፤ በኤ​ር​ገብ ድን​ጋ​ይም አጠ​ገብ ቈይ።