የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




1 ነገሥት 2:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

አንተ ግን ጥበ​በኛ ሰው ነህና ንጹሕ አታ​ድ​ር​ገው፤ የም​ታ​ደ​ር​ግ​በ​ት​ንም አንተ ታው​ቃ​ለህ፤ ሽበ​ቱ​ንም በደም ወደ መቃ​ብር አው​ር​ደው” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

አሁን ግን በደል እንደሌለበት ሰው አትተወው፤ ጥበበኛ ነህና መደረግ ያለበትን ታውቃለህ፤ ሽበቱን በደም ወደ መቃብር አውርድ።”

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

አንተ ግን እርሱንም ከቅጣት ነጻ አታድርገው፤ ባለህ ጥበብ ምን መደረግ እንዳለበት አንተ ራስህ ታውቃለህ፤ በሞት የሚቀጣ መሆኑንም አትዘንጋ።”

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አንተ ግን እርሱንም ከቅጣት ነጻ አታድርገው፤ ባለህ ጥበብ ምን መደረግ እንዳለበት አንተ ራስህ ታውቃለህ፤ በሞት የሚቀጣ መሆኑንም አትዘንጋ።”

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

አንተ ግን ጥበበኛ ሰው ነህና ያለ ቅጣት አትተወው፤ የምታደርግበትንም አንተ ታውቃለህ፤ ሽበቱንም ከደም ጋር ወደ መቃብር አውርድ።”

ምዕራፉን ተመልከት



1 ነገሥት 2:9
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እር​ሱም አለ፥ “ልጄ ከእ​ና​ንተ ጋር አይ​ወ​ር​ድም፤ ወን​ድሙ ሞቶ እርሱ ብቻ ቀር​ቶ​አ​ልና፤ በም​ት​ሄ​ዱ​በት መን​ገድ ምና​ል​ባት ክፉ ነገር ቢያ​ገ​ኘው ሽም​ግ​ል​ና​ዬን በኀ​ዘን ወደ መቃ​ብር ታወ​ር​ዱ​ታ​ላ​ችሁ።”


ብላ​ቴ​ናው ከእኛ ጋር እን​ደ​ሌለ በአየ ጊዜ ይሞ​ታል፤ አገ​ል​ጋ​ዮ​ች​ህም የአ​ገ​ል​ጋ​ይ​ህን የአ​ባ​ታ​ች​ንን እር​ጅና በኀ​ዘን ወደ መቃ​ብር እና​ወ​ር​ዳ​ለን።


የሰ​ውን ደም የሚ​ያ​ፈ​ስስ ሁሉ ስለ​ዚያ ደም ፈንታ ደሙ ይፈ​ስ​ሳል፤ ሰውን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መልክ ፈጥ​ሬ​ዋ​ለ​ሁና።


ንጉሡ ዳዊ​ትም ወደ በው​ሪም መጣ፤ እነ​ሆም፥ ሳሚ የሚ​ባል የጌራ ልጅ ከሳ​ኦል ቤተ ዘመድ የሆነ አንድ ሰው ከዚያ ወጣ፤ እየ​ሄ​ደም ይረ​ግ​መው ነበር።


እኔም ዛሬ ዘመዱ እንደ ሆንሁ፥ እር​ሱም በን​ጉሡ ዘንድ የተ​ሾመ እንደ ሆነ አታ​ው​ቁ​ምን? እነ​ዚ​ህም ሰዎች የሦ​ር​ህያ ልጆች በር​ት​ተ​ው​ብ​ኛል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክፋት በሠራ ላይ እንደ ክፋቱ ይመ​ል​ስ​በት” አላ​ቸው።


አን​ተም እንደ ጥበ​ብህ አድ​ርግ፤ ሽበ​ቱ​ንም በሰ​ላም ወደ መቃ​ብር አታ​ው​ር​ደው።


እነሆ፥ እኔ እንደ ቃልህ አድ​ር​ጌ​ል​ሃ​ለሁ፤ እነ​ሆም፥ ማንም የሚ​መ​ስ​ልህ ከአ​ንተ በፊት እን​ደ​ሌለ፥ ከአ​ን​ተም በኋላ እን​ዳ​ይ​ነሣ አድ​ርጌ ጥበ​በ​ኛና አስ​ተ​ዋይ ልቡና ሰጥ​ቼ​ሃ​ለሁ።


ንጉ​ሡም የፈ​ረ​ደ​ውን ፍርድ እስ​ራ​ኤል ሁሉ ሰሙ፤ ፍር​ድን ለማ​ድ​ረግ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጥበብ በእ​ርሱ ላይ እንደ ነበረ አይ​ተ​ዋ​ልና ከን​ጉሡ ፊት የተ​ነሣ ፈሩ።


ሰው​ነ​ቶቼ ሁሉ ተነ​ዋ​ወጡ፤ እን​ግ​ዲህ ንጹሕ አድ​ር​ገህ እን​ደ​ማ​ት​ተ​ወኝ አው​ቃ​ለሁ፥


“የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የአ​ም​ላ​ክ​ህን ስም በከ​ንቱ አት​ጥራ፤ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስሙን በከ​ንቱ የሚ​ጠ​ራ​ውን ከበ​ደል አያ​ነ​ጻ​ው​ምና።


ልብሱ ነውና፥ ዕር​ቃ​ኑ​ንም የሚ​ሸ​ፍ​ን​በት ይህ ብቻ ነውና፤ የሚ​ተ​ኛ​በ​ትም ሌላ የለ​ው​ምና፤ ወደ እኔም ቢጮኽ ፈጥኜ እሰ​ማ​ዋ​ለሁ፤ መሓሪ ነኝና።


“ፈራ​ጆ​ችን አት​ስ​ደብ፥ የሕ​ዝ​ብ​ህ​ንም አለቃ ክፉ አት​ና​ገ​ረው።


እን​ዲህ ባታ​ደ​ርጉ ግን፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ትበ​ድ​ላ​ላ​ችሁ፤ ክፉ ነገር ባገ​ኛ​ችሁ ጊዜ በደ​ላ​ች​ሁን ታው​ቃ​ላ​ችሁ።