በዐይኖችም በተመለከትሁ ጊዜ በቀኝ በኩል እነሆ፥ አንዲት የምታለቅስ ሴትን አየሁ፤ በታላቅ ድምፅም ትጮኽ ነበር፤ እጅግም አዝና ነበር፤ ልብሷም ተቀድዶ ነበር፤ በራሷም ላይ ዐመድ ነስንሳ ነበር።