እኔስ አልተዋችሁም፤ ከእናንተም አልርቅም፤ ነገር ግን ወደዚህ ቦታ የመጣሁት ስለ ጽዮን ጥፋት እለምን ዘንድ ነው፤ በደስታችን ላይ ስለ መጣብንም መከራ ይቅርታን እለምን ዘንድ ነው።