የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




1 ቆሮንቶስ 5:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እና​ን​ተም ከዚህ ጋር ትዕ​ቢ​ተ​ኞች ናችሁ፤ ይል​ቁ​ንም ይህን ያደ​ረ​ገው ከእ​ና​ንተ ይለይ ዘንድ ለምን አላ​ዘ​ና​ች​ሁ​በ​ትም?

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ደግሞም ታብያችኋል! ይልቅስ ሐዘን ተሰምቷችሁ፣ ይህን ድርጊት የፈጸመውን ሰው ከመካከላችሁ ልታስወግዱት አይገባምን?

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እናንተም ታብያችኋል፤ ይልቅስ ልታዝኑ አይገባችሁም? ይህን ሥራ የሠራው ከመካከላችሁ ይወገድ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ታዲያ፥ እንዲህ ያለ አሳፋሪ ነገር በመካከላችሁ እያለ ለምን ትታበያላችሁ? ይልቅስ በዚህ ነገር ማዘን አይገባችሁምን? እንዲህ ዐይነቱን ሥራ የፈጸመውን ሰው ከመካከላችሁ አስወግዱ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እናንተም ታብያችኋል፤ ይልቅስ እንድታዝኑ አይገባችሁምን? ይህን ሥራ የሠራው ከመካከላችሁ ይወገድ።

ምዕራፉን ተመልከት



1 ቆሮንቶስ 5:2
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ልብ​ህን አላ​ደ​ነ​ደ​ን​ህ​ምና፥ እነ​ር​ሱም ለጥ​ፋ​ትና ለመ​ር​ገም እን​ዲ​ሆኑ በዚህ ስፍ​ራና በሚ​ኖ​ሩ​በት ላይ የተ​ና​ገ​ር​ሁ​ትን ሰም​ተህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ተዋ​ር​ደ​ሃ​ልና፥ ልብ​ስ​ህን ቀድ​ደ​ሃ​ልና፥ በፊ​ቴም አል​ቅ​ሰ​ሃ​ልና እኔ ደግሞ ሰም​ቼ​ሃ​ለሁ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ይህን ባት​ሰሙ ነፍሴ ስለ ትዕ​ቢ​ታ​ችሁ በስ​ውር ታለ​ቅ​ሳ​ለች፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መንጋ ተሰ​ብ​ሮ​አ​ልና ዐይኔ ታነ​ባ​ለች፤ እን​ባ​ንም ታፈ​ስ​ሳ​ለች።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “በከ​ተ​ማ​ዪቱ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም መካ​ከል እለፍ፥ በመ​ካ​ከ​ል​ዋም ስለ ተሠ​ራው ኀጢ​አት ሁሉ በሚ​ያ​ለ​ቅ​ሱና በሚ​ተ​ክዙ ሰዎች ግን​ባር ላይ ምል​ክት ጻፍ አለው።


ሽማ​ግ​ሌ​ው​ንና ጎበ​ዙን፥ ድን​ግ​ሊ​ቱ​ንም፥ ሕፃ​ና​ቱ​ንና ሴቶ​ቹን፥ ፈጽ​ማ​ችሁ ግደሉ፤ ነገር ግን ምል​ክቱ ወደ አለ​በት ሰው ሁሉ አት​ቅ​ረቡ፤ በመ​ቅ​ደ​ሴም ጀምሩ” አላ​ቸው። በቤ​ቱም አን​ጻር ባሉ ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ጀመሩ።


እነ​ሆም፥ ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች አንዱ መጥቶ በሙ​ሴና በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ማኅ​በር ሁሉ ፊት ወን​ድ​ሙን ወደ ምድ​ያ​ማ​ዊት ሴት ወሰ​ደው፤ እነ​ር​ሱም በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ዳጃፍ ያለ​ቅሱ ነበር።


እነሆ፥ ወደ እና​ንተ ስላ​ል​መ​ጣሁ ከእ​ና​ንተ ወገን የታ​በዩ ሰዎች አሉ።


በውጭ ያሉ​ትን ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይፈ​ር​ድ​ባ​ቸ​ዋል፤ ይቀ​ጣ​ቸ​ዋ​ልም፤ ክፉ​ውን ከእ​ና​ንተ አርቁ።


ነገር ግን ወደ እና​ንተ በመ​ጣሁ ጊዜ እን​ደ​ም​ወ​ደው ሆና​ችሁ ያላ​ገ​ኘ​ኋ​ችሁ እንደ ሆነ፤ እኔም እን​ደ​ማ​ት​ወ​ዱት እሆ​ን​ባ​ች​ኋ​ለሁ ብዬ እፈ​ራ​ለሁ፤ ወይም እኮ በመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ ክር​ክር፥ ኵራት፥ መቀ​ና​ናት፥ መበ​ሳ​ጨት፥ መዘ​ባ​በት፥ ወይም መተ​ማ​ማት፥ መታ​ወክ፥ ወይም ልብን ማስ​ታ​በይ ይኖር ይሆ​ናል።


ወይም እንደ ገና ወደ እና​ንተ በመ​ጣሁ ጊዜ በእ​ና​ንተ ምክ​ን​ያት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያሳ​ዝ​ነኝ ይሆ​ናል፤ በድ​ለው ንስሓ ላል​ገ​ቡም ስለ ርኵ​ስ​ነ​ታ​ቸ​ውና ስለ መዳ​ራ​ታ​ቸው፥ ስለ​ሚ​ሠ​ሩት ዝሙ​ታ​ቸ​ውም ለብ​ዙ​ዎች አዝን ይሆ​ናል።