መዝሙር 66:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ያደረገልኝን ሁሉ እንድነግራችሁ፥ እግዚአብሔርን የምትፈሩ ሁሉ ኑ ስሙ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔርን የምትፈሩ ሁሉ፤ ኑና ስሙ፤ ለነፍሴ ያደረገላትን ልንገራችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግዚአብሔርን የምትፈሩት ሁሉ፥ ኑ፥ ስሙኝ፥ ለነፍሴ ያደረገላትን ልንገራችሁ። |
እስራኤላውያን እንዲህ ተባባሉ፦ “እግዚአብሔር ለእኛ ትክክለኛ ፍርዱን ስለ ሰጠን ኑ! ወደ ኢየሩሳሌም ሄደን እግዚአብሔር አምላካችን ያደረገውን ሁሉ እንናገር።”
ከዚያ በኋላ እግዚአብሔርን የሚያከብሩ ሰዎች እርስ በርሳቸው ተነጋገሩ፤ እግዚአብሔርም በጥሞና አዳመጣቸው፤ እግዚአብሔርን የሚፈሩና ስሙንም የሚያከብሩ ሰዎች ለተግባራቸው መታሰቢያ በመጽሐፍ ተጻፈ።
ከእኛ ጋር አንድነት እንዲኖራችሁ ያየነውንና የሰማነውን ለእናንተም እንነግራችኋለን። አንድነታችንም ከአብና ከልጁም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ነው።